Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 20:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እስቲ ንገረን! በሕጋችን መሠረት ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር መክፈል ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም?”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ለቄሣር ግብር እንድንሰጥ ተፈቅዶአልን? ወይስ አልተፈቀደም?” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ለቄ​ሣር ግብር መስ​ጠት ይገ​ባል? ወይስ አይ​ገ​ባም?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ለቄሣር ግብር ልንሰጥ ተፈቅዶአልን? ወይስ አልተፈቀደም? አሉት።

参见章节 复制




ሉቃስ 20:22
14 交叉引用  

ስለዚህም ንጉሥ ሆይ! ይህች ከተማ እንደገና ከተሠራችና የቅጽሮችዋም ሥራ ከተጠናቀቀ፥ ሕዝቡ ግብር መክፈላቸውን ያቆማሉ፤ ለግርማዊነትዎ የሚቀርበውም የንጉሣዊ ቤተ መንግሥት ገቢ ሊቀነስ የሚችል መሆኑን ይታወቅ፤


ከቀድሞ አባቶቻችን ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እኛ ታላቅ በደል ሠርተናል፤ ከኃጢአታችንም ብዛት የተነሣ እኛ፥ ነገሥታቶችንና ካህናታችን በባዕዳን ነገሥታት እጅ ወድቀናል፤ ስለዚህም ለሰይፍ ተዳረግን፤ ሀብታችንንም ተዘረፍን፤ በመታሰር ተማርከን ተወሰድን፤ እነሆ፥ አሁንም እንዳለንበት ሁኔታ እስከ መጨረሻ ተዋርደናል።


ሌሎችም ደግሞ “ስለ እርሻችንና ስለ ወይን ተክላችን መንግሥት የጠየቀንን ግብር ለመክፈል የገንዘብ ብድር ተበድረናል፤


እኛም ኃጢአት በመሥራታችን ምክንያት ስላሳዘንክ፥ የምድሪቱንም በረከት በእኛ ላይ ገዢዎች አድርገህ ላስነሣሃቸው ነገሥታት ገቢ ይሆናል፤ እነርሱ በእኛና በእንስሶቻችን ላይ ደስ ያሰኛቸውን ነገር ሁሉ ይፈጽማሉ፤ ከዚህም የተነሣ፥ በታላቅ ጭንቀት ላይ እንገኛለን።”


ጴጥሮስም “ኧረ ይከፍላል” አላቸው። ጴጥሮስ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ኢየሱስ አስቀድሞ “ስምዖን ጴጥሮስ ሆይ! ምን ይመስልሃል? የዚህ ዓለም መንግሥታት ቀረጥና ግብር የሚቀበሉት ከማን ነው? ከልጆቻቸው ነውን ወይስ ከውጪ አገር ሰዎች?” ሲል ጠየቀው።


ሰላዮቹም ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤ “መምህር ሆይ! አንተ የምትናገረውና የምታስተምረው እውነት መሆኑን እናውቃለን፤ የእግዚአብሔርን መንገድ በእውነት ታስተምራለህ እንጂ ለማንም አታዳላም።


ኢየሱስ ግን ተንኰላቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤


እንዲህ እያሉም ይከሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት አገኘነው፤ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር እንዳይከፈል ይከለክላል፤ ደግሞ ‘እኔ ንጉሥ መሲሕ ነኝ’ እያለ ይናገራል።”


ከዚያም በኋላ የሕዝብ ቈጠራ በተደረገበት ዘመን ገሊላዊው ይሁዳ ተነሥቶ ብዙ ሰዎች እንዲከተሉት አድርጎ ነበር፤ እርሱም ተገደለ፤ የተከተሉትም ሁሉ ተበታተኑ።


እንግዲህ ለበላይ ባለሥልጣን ሊደረግ የሚገባውን ሁሉ አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ክፈሉ፤ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።


እግዚአብሔር አምላክህ የሚመርጥልህን ንጉሥ ልታነግሥ ትችላለህ፤ በአንተም ላይ የምታነግሠው ንጉሥ ከወገንህ መካከል ይሁን፥ ከወገንህ ያልሆነውን የውጪ አገር ሰው ልታነግሥ አይገባህም።


跟着我们:

广告


广告