Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 18:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ቀድመው እፊት እፊት ይሄዱ የነበሩት ሰዎች፦ “ዝም በል!” ብለው ገሠጹት። እርሱ ግን ድምፁን በይበልጥ ከፍ አድርጎ፦ “የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” ይል ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ከፊት የሚሄዱ ሰዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፣ “የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ የባሰ ጮኸ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 በስተ ፊት ይሄዱ የነበሩትም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረኝ፤” እያለ አብዝቶ ጮኸ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 የሚ​መ​ሩ​ትም ዝም እን​ዲል ገሠ​ጹት፤ እርሱ ግን በጣም ጮኾ፥ “የዳ​ዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 በስተ ፊት ይሄዱ የነበሩትም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፦ የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ።

参见章节 复制




ሉቃስ 18:39
16 交叉引用  

እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ እጣራለሁ፤ በፍጥነትም እርዳኝ! ወደ አንተም ስጮኽ ስማኝ!


“ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤


እርሱም “እናንተ እምነት የጐደላችሁ! ስለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው። ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።


ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ተነሥቶ ሲሄድ ሁለት ዕውሮች ተከተሉት፤ እነርሱም “የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረን!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


“እናንተ የሕግ መምህራን ወዮላችሁ! የዕውቀት በር መክፈቻ የሆነውን የእውነት ቊልፍ ይዛችኋል፤ ነገር ግን እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁበትም፤ መግባት የሚፈልጉትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።”


ከዚህ በኋላ፥ ኢየሱስ ሳይታክቱ ዘወትር መጸለይ እንደሚገባቸው ለማስተማር ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤


ኢየሱስ እንዲዳስሳቸው ሰዎች ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ይህን ባዩ ጊዜ ሰዎቹን ተቈጡአቸው።


በዚያን ጊዜ ዐይነ ስውሩ፥ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” እያለ ጮኸ።


ስለዚህ ኢየሱስ ቆመና “ወደ እኔ አምጡት” ብሎ አዘዘ። ዐይነ ስውሩም ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ፥ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦


በሕዝቡ መካከል የነበሩት አንዳንድ ፈሪሳውያን ግን ኢየሱስን “መምህር ሆይ! ደቀ መዛሙርትህን ዝም አሰኛቸው!” አሉት።


ኢየሱስ ገና ይህንን በመናገር ላይ ሳለ አንድ ሰው ከምኲራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን በከንቱ አታድክመው!” አለው።


ይህ የሚያሠቃየኝ ነገር ከእኔ እንዲወገድልኝ ጌታን ሦስት ጊዜ ለመንኩት።


跟着我们:

广告


广告