Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 18:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ሰውየው ግን በጣም ሀብታም ስለ ነበረ፥ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ሰውየው ግን ይህን ሲሰማ፣ ብዙ ሀብት ስለ ነበረው በጣም ዐዘነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እርሱ ግን እጅግ ሀብታም ነበርና ይህንን ሰምቶ በጣም አዘነ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እርሱ ግን ይህን ሰምቶ በጣም አዘነ፤ እርሱ እጅግ ባለ​ጸጋ ነበ​ርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እርሱ ግን ይህን ሰምቶ እጅግ ባለ ጠጋ ነበርና ብዙ አዘነ።

参见章节 复制




ሉቃስ 18:23
15 交叉引用  

ስለዚህም ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሕዝቤ አንተ ምን እንደምትናገር ለማዳመጥ ብቻ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የምትነግራቸውን ሁሉ አይፈጽሙም፤ የምትናገረውን ቃል የሚወዱት መስለው ይታያሉ፤ ነገር ግን ከበዝባዥነታቸው አይመለሱም፤


ወጣቱ ግን ብዙ ሀብት ስለ ነበረው ይህን በሰማ ጊዜ እየተከዘ ሄደ።


ሰውየውም ይህን በሰማ ጊዜ ፊቱ በሐዘን ጠቈረ፤ ብዙ ንብረትም ስለ ነበረው እያዘነ ሄደ።


ቀጥሎ ለሁሉም እንዲህ አላቸው፤ “የሰው ሕይወት በሀብቱ ብዛት አይደለም፤ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ከስስትም ተጠበቁ።”


ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ ሰውየውን፥ “እንግዲያውስ ገና አንድ ነገር ማድረግ ይቀርሃል፤ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ገንዘቡን ለድኾች ስጥ፤ በሰማይ የተከማቸ ሀብት ታገኛለህ፤ ከዚያም በኋላ መጥተህ ተከተለኝ” አለው።


ኢየሱስም ሰውየው እንዳዘነ አይቶ፥ እንዲህ አለ፤ “ለሀብታሞች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት አስቸጋሪ ነው!


ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታ ኢየሱስን እንዲህ አለው፦ “ጌታ ሆይ! እነሆ፥ ካለኝ ሀብት ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ በማታለል ከሰው ላይ የወሰድኩትም ገንዘብ ቢኖር፥ አራት እጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ።”


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።


በእሾኽም ቊጥቋጦ መካከል የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ለጊዜው የሚሰሙትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን የዚህ ዓለም ሐሳብና ሀብት፥ የምድራዊ ኑሮ ምቾትም አንቆ ያለ ፍሬ ያስቀራቸዋል።


አመንዝራም ቢሆን፥ ማናቸውንም የርኲሰት ሥራ የሚያደርግ ቢሆን፥ ወይም ጣዖት እንደ ማምለክ የሆነ ስግብግብነት ቢሆን፥ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደማያገኝ ዕወቁ።


ከዚህም በቀር ጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስን ከማወቅ የበለጠ ሌላ ምንም ነገር እንደሌለ ስለማምን ሁሉን ነገር እንደ ኪሣራ እቈጥረዋለሁ፤ ስለ እርሱም ሁሉን ነገር አጥቻለሁ። ክርስቶስንም ለማግኘት ስል ሁሉን ነገር እንደ ቤት ጥራጊ እቈጥራለሁ።


ስለዚህ በእናንተ የሚገኙትን የምድራዊ ሕይወት ምኞቶች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም “ዝሙት፥ ርኲሰት፥ ፍትወት፥ ክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማምለክ የሆነ መጐምጀት” ናቸው።


ዓለምን ወይም የዓለምን ነገር ሁሉ አትውደዱ። ዓለምን የሚወድ እግዚአብሔር አብን አይወድም።


跟着我们:

广告


广告