Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 17:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ከእናንተ አንዱ በእርሻ ሥራ የተሰማራ፥ ወይም በጎች የሚጠብቅ አገልጋይ ቢኖረው፥ አገልጋዩ ከሥራው በተመለሰ ጊዜ ወዲያውኑ ‘ና ተቀመጥና ራትህን ብላ’ ይለዋልን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ከእናንተ መካከል አንድ ሰው ዐራሽ ወይም በግ ጠባቂ የሆነ ባሪያ ቢኖረው፣ ከዕርሻ የተመለሰውን ባሪያውን፣ ‘ቶሎ ወደ ማእድ ቅረብ’ ይለዋልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ አገልጋይ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ ‘ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ፤’ የሚለው ማን ነው?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “አራሽ ወይም ከብት ጠባቂ አገ​ል​ጋይ ያለው ከእ​ና​ንተ ማን ነው? ከእ​ር​ሻው በተ​መ​ለሰ ጊዜ ጌታው ና፥ ፈጥ​ነህ ወደ​ዚህ ውጣና ከእኔ ጋር በማ​ዕድ ተቀ​መጥ ይለ​ዋ​ልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ ባሪያ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ፦ ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ የሚለው ማን ነው?

参见章节 复制




ሉቃስ 17:7
6 交叉引用  

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ መካከል አንድ በግ ያለው፥ በጉ በሰንበት ቀን በጒድጓድ ውስጥ ቢወድቅበት ስቦ የማያወጣው ማነው?


ጌታ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተስ እያንዳንዱ በሰንበት ቀን በሬውን ከተዘጋበት አውጥቶ፥ ወይም አህያውን ከታሰረበት ፈቶ ውሃ ወደሚያጠጣበት ቦታ ይወስደው የለምን?


ቀጥሎም ኢየሱስ፦ “ከእናንተ በሰንበት ቀን ልጁ ወይም በሬው በጒድጓድ ውስጥ ቢወድቅበት ወዲያውኑ የማያወጣው ማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው።


በኖኅ ዘመን እንደሆነው ዐይነት የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜም እንዲሁ ይሆናል።


ጌታ ኢየሱስም “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያኽል እምነት ቢኖራችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ በባሕር ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዝላችኋል” አላቸው።


ይልቅስ፥ ‘በል! ራቴን አዘጋጅልኝ፤ እስክበላና እስክጠጣም አደግድገህ አገልግለኝ፤ ከዚህ በኋላ አንተ ደግሞ ትበላለህ፥ ትጠጣለህ’ ይለው የለምን?


跟着我们:

广告


广告