Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 14:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በሰንበት ቀን፥ ኢየሱስ ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት ምሳ ሊበላ ገባ፤ ፈሪሳውያን እርሱ የሚያደርገውን ለማየት ይጠባበቁት ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አንድ ሰንበት ቀን፣ ኢየሱስ ምግብ ሊበላ ከፈሪሳውያን አለቆች አንዱ ወደ ነበረ ሰው ቤት በገባ ጊዜ፣ ሰዎች በዐይን ይከታተሉት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሰንበትም ቀን ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት ምግብ ሊበላ በገባ ጊዜ እነርሱ ይጠባበቁት ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ ሄዶ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን አለ​ቆች ወደ አንዱ ቤት በሰ​ን​በት ቀን እህል ሊበላ ገባ፤ እነ​ርሱ ግን ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሰንበትም ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት እንጀራ ሊበላ በገባ ጊዜ እነርሱ ይጠባበቁት ነበር።

参见章节 复制




ሉቃስ 14:1
19 交叉引用  

ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ይሸምቃል፤ ሊገድለውም ይፈልጋል።


እኔን ለመጐብኘት የሚመጡት ከልባቸው አይደለም፤ በእኔ ላይ መጥፎ ወሬ ይሰበስባሉ፤ በየቦታውም እየዞሩ ስሜን ያጠፋሉ።


እነርሱ የሚፈልጉት ክብሩን ለመሻር ስለ ሆነ በእርሱ ላይ ሐሰት መናገርን ይወዳሉ፤ በአፋቸው ይመርቁታል፤ በልባቸው ግን ይረግሙታል።


ከልቡ ሳይሆን ምግቡን እንድትተውለት ፈልጎ ለማስመሰል ያኽል “ብላ፥ ጠጣ” ይልሃል።


ታዲያ፥ ከበግ ይልቅ ሰው እንዴት አይበልጥም! ስለዚህ በሰንበት ቀን መልካም ነገር ማድረግ የተፈቀደ ነው።”


ኢየሱስን ሊከሱት የፈለጉ ሰዎች፥ “እስቲ በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደ ሆነ እንይ!” ብለው ይጠባበቁት ነበር።


ኢየሱስ ይህን በሚናገርበት ጊዜ አንድ ፈሪሳዊ ምሳ ጋበዘው፤ ወደ ፈሪሳዊው ቤት ገብቶ ምሳ ለመብላት ወደ ማእድ ቀረበ።


በዚያን ጊዜ በሕመም ምክንያት መላ ሰውነቱ ያበጠበት አንድ ሰው በኢየሱስ ፊት ነበር።


ፈሪሳውያን ኢየሱስን፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች?” ሲሉ ጠየቁት፤ እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የእግዚአብሔር መንግሥት የምትመጣው ሰዎች ነቅተው በሚጠባበቁት ዐይነት አይደለም፤


ስለዚህ ኢየሱስን ለመያዝ ምቹ ጊዜ ይጠብቁ ነበር። ለገዥው ሥልጣንና ፍርድ አሳልፈው ለመስጠት የሚያስችላቸውን የወንጀል ቃል ከእርሱ ለማግኘት ይፈልጉ ነበር፤ ስለዚህ ቅን ሰዎች መስለው፥ በንግግሩ የሚያጠምዱትን ሰላዮች ላኩበት።


የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያንም ኢየሱስን የሚከሱበት ወንጀል ለማግኘት ፈልገው፥ “እስቲ በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደ ሆነ እንይ፤” ብለው ይጠባበቁት ነበር።


ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱ ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ ነበረ።


ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ የተከበረና የሕግ መምህር የሆነ፥ ገማልያል የተባለ አንድ ፈሪሳዊ የሸንጎ አባል ተነሣና ለጥቂት ጊዜ ሐዋርያቱን ገለል እንዲያደርጉአቸው አዘዘ።


跟着我们:

广告


广告