Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 12:58 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

58 ባላጋራህ ከሶህ ወደ ፍርድ ቤት በሚወስድህ ጊዜ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ለመስማማት ተጣጣር፤ አለበለዚያ እርሱ ወደ ዳኛ ጐትቶ ይወስድሃል፤ ዳኛውም ለአሳሪው አሳልፎ ይሰጥሃል፤ አሳሪውም ወደ እስር ቤት ያገባሃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

58 ከባላጋራህ ጋራ ወደ ዳኛ ፊት ለመቅረብ ስትሄድ፣ ገና በመንገድ ላይ ሳለህ ለመታረቅ ጥረት አድርግ፤ አለዚያ ጐትቶ ወደ ዳኛው ይወስድሃል፤ ዳኛውም ለመኰንኑ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ መኰንኑም ወደ ወህኒ ይጥልሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

58 ከባላጋራህ ጋር ወደ ሹም ብትሄድ፥ ወደ ዳኛ እንዳይጐትትህ ዳኛውም ለሎሌው አሳልፎ እንዳይሰጥህ ሎሌውም በወኅኒ እንዳይጥልህ፥ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ለመታረቅ ትጋ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

58 ከባ​ለ​ጋ​ራህ ጋር ወደ ሹም በም​ት​ሄ​ድ​በት ጊዜ ወደ ዳኛ እን​ዳ​ይ​ወ​ስ​ድህ በመ​ን​ገድ ሳለህ ታረቅ፤ ዕዳ​ህ​ንም ክፈል፤ ዳኛው ለሎ​ሌው አሳ​ልፎ ይሰ​ጥ​ሃ​ልና። ሎሌ​ውም በወ​ኅኒ ቤት ያስ​ር​ሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

58 ከባላጋራህ ጋር ወደ ሹም ብትሄድ፥ ወደ ዳኛ እንዳይጐትትህ ዳኛውም ለሎሌው አሳልፎ እንዳይሰጥህ ሎሌውም በወኅኒ እንዳይጥልህ፥ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ እንድትታረቅ ትጋ።

参见章节 复制




ሉቃስ 12:58
20 交叉引用  

“ስለዚህ ኢዮብ ሆይ፥ ራስህን ለእግዚአብሔር አስገዛ፤ ከእርሱም ጋር ሰላም ይኑርህ፤ ይህን ብታደርግ መልካም ነገርን ታገኛለህ።


በዚያ ቅን ሰው ከእርሱ ጋር ይከራከራል፤ ዳኛዬ እግዚአብሔርም ለዘለዓለም ነጻ ያወጣኛል።


ስለዚህ በጭንቀት ሰዓት እያንዳንዱ ለአንተ ታማኝ ሰው ወደ አንተ ይጸልይ፤ ብርቱ የመከራ ጐርፍ በሚመጣበት ጊዜ እርሱን አይነካውም።


“ስለዚህ እናንተ እኔን የምትንቁ ሁሉ ይህን አስተውሉ፤ አለበለዚያ አጠፋችኋለሁ፤ የሚያድናችሁም የለም።


በሚገኝበት ጊዜ እግዚአብሔርን ፈልጉት፤ በሚቀርብበትም ጊዜ ጥሩት።


ሰውየው ግን እምቢ አለው። እንዲያውም ይዞት ሄደና ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወህኒ ቤት አሳሰረው።


እግዚአብሔር፦ “ተስማሚ በሆነ ጊዜ ሰማሁህ! በመዳን ቀን ረዳሁህ!” ስለሚል፥ “እነሆ ተስማሚ የሆነው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳኛው ቀን አሁን ነው።”


በዚያው መንፈስ በእስር ቤት ወዳሉት ነፍሶች ሄዶ የምሥራቹን ቃል አበሠራቸው።


እኔ አሁን የምተጋው በሞት ከተለየኋችሁ በኋላ እንኳ እነዚህን ነገሮች ዘወትር ማስታወስ እንድትችሉ ነው።


ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ በብርቱ ፈልጌ ነበር፤ አሁን ግን በማያዳግም ሁኔታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ አንድ ጊዜ ስለ ሰጠው እምነት በብርቱ እንድትጋደሉ ለመምከር ልጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።


ሺህ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፤


跟着我们:

广告


广告