Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 10:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ለመንገዳችሁ ምንም አትያዙ፤ የገንዘብ ቦርሳም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ ጫማም ቢሆን አትያዙ፤ ከሰው ጋር ሰላምታ በመለዋወጥ በመንገድ ላይ ቆማችሁ ጊዜ አታጥፉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ኰረጆ ወይም ከረጢት ወይም ጫማ አትያዙ፤ በመንገድ ላይም ለማንም ሰላምታ አትስጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ቦርሳም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድ ላይ ለማንም ሰላምታን አትስጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከረ​ጢ​ትም፥ ስል​ቻም፥ ጫማም፥ ምንም ምን አት​ያዙ፤ በመ​ን​ገ​ድም ማን​ንም ሰላም አት​በሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ኮረጆም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድም ለማንም እጅ አትንሡ።

参见章节 复制




ሉቃስ 10:4
13 交叉引用  

ገበታ በቀረበ ጊዜ ሰውየው “የተላክሁበትን ጉዳይ ከመናገሬ በፊት እህል አልቀምስም” አለ። ላባም “ይሁን ተናገር” አለው።


እርሱ ግን “እባካችሁ አታቈዩኝ፤ እግዚአብሔር የመጣሁበትን ጉዳይ ስላቃናልኝ ቶሎ ብዬ ወደ ጌታዬ ልመለስ” አላቸው።


እርስዋም አህያው እንዲጫንላት ካደረገች በኋላ አገልጋዩን “በሚቻል መጠን አህያው እንዲፈጥን አድርግ፤ እኔም ካልነገርኩህ በቀር ቀስ ብሎ እንዲሄድ ፋታ አትስጠው” ስትል አዘዘችው።


ኤልሳዕም ወደ ግያዝ መለስ ብሎ “በፍጥነት ተነሥና የእኔን ምርኲዝ ይዘህ ሂድ! ለአንድም ሰው ሰላምታ ለመስጠት እንኳ በመንገድ አትቁም፤ ማንም ሰው ሰላምታ ቢሰጥህ አጸፋውን ለመመለስ ጊዜ አታጥፋ፤ በቀጥታ ወደ ቤት ሄደህ የእኔን ምርኲዝ በልጁ ፊት ላይ አኑር!” አለው።


አመለካከትህ ቀጥተኛ ይሁን፤ ግራና ቀኝ ሳትል ወደፊት ተመልከት።


ዐሥራ ሁለቱን ወደ እርሱ ጠርቶ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው፤ በርኩሳን መናፍስትም ላይ ሥልጣን ሰጣቸው፤


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “የገንዘብ ቦርሳ፥ ከረጢት፥ ጫማም ሳትይዙ በላክኋችሁ ጊዜ የጐደለባችሁ ነገር ነበርን?” አላቸው። እነርሱም “ምንም የጐደለብን ነገር አልነበረም” ሲሉ መለሱለት።


ዳዊትም አቤሜሌክን “የምትሰጠኝ ጦር ወይም ሰይፍ በአንተ ዘንድ ይገኛልን? የንጉሡ ትእዛዝ አስቸኳይ ስለ ሆነ ጦሬንም ሆነ ሌላውንም መሣሪያዬን ለመያዝ ጊዜ አላገኘሁም ነበር” አለው።


跟着我们:

广告


广告