Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 1:65 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

65 ከዚህም የተነሣ በጐረቤቶቻቸው ሁሉ ፍርሀት አደረባቸው፤ ዜናውም በተራራማው በይሁዳ ምድር ሁሉ ተሰማ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

65 ጎረቤቶቹም ሁሉ በፍርሀት ተሞሉ፤ ይህም ሁሉ ነገር በደጋማው የይሁዳ ምድር ሁሉ ተወራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

65 በጎረቤቶቻቸውም ሁሉ ላይ ፍርሃት ሆነ፤ ይህም ሁሉ ነገር በተራራማው በይሁዳ አገር ሁሉ ተወራ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

65 በዚ​ያም ሀገር ሰው ሁሉ ላይ ፍር​ሀት ሆነ፤ ይህም ነገር ሁሉ በይ​ሁዳ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሁሉ ተወራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

65 ለጎረቤቶቻቸውም ሁሉ ፍርሃት ሆነ፤ ይህም ሁሉ ነገር በይሁዳ በተራራማው አገር ሁሉ ተወራ፤

参见章节 复制




ሉቃስ 1:65
12 交叉引用  

በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን፥ በይሁዳ ምድር በምትገኝ በቤተልሔም ከተማ ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


በዚያን ጊዜ ማርያም በተራራማው በይሁዳ አገር ወዳለችው ከተማ በፍጥነት ተነሥታ ሄደች።


ይህንንም የሰሙ ሁሉ እረኞቹ ባወሩላቸው ነገር ተደነቁ።


በዚያም የነበሩ ሰዎች ሁሉ እጅግ ተገርመው፥ በመፍራት፥ “ዛሬ ድንቅ ነገር አየን፤” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


ሁሉንም ፍርሀት ይዞአቸው፥ “ታላቅ ነቢይ ከመካከላችን ተነሥቶአል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊያድን መጥቶአል፤” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


ይህም ነገር በኤፌሶን በሚኖሩት አይሁድና አሕዛብ ዘንድ ስለ ተሰማ ሁሉም ፈሩ፤ የጌታ የኢየሱስም ስም እጅግ ገናና ሆነ።


በዚያን ጊዜ በሐዋርያት እጅ ብዙ ተአምራትና ድንቅ ነገሮች ይደረጉ ስለ ነበር በሁሉም ላይ ፍርሀት ዐደረባቸው።


በቤተ ክርስቲያን ሁሉና ይህን ነገር በሰሙ ሰዎች ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሀት ሆነ።


ሐናንያ ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ወደቀና ሞተ፤ ይህን ነገር የሰሙ ሰዎች ሁሉ እጅግ ፈሩ።


በዚህ ዐይነት ኢያሱ ምድሪቱን በሙሉ፥ የተራራማውን አገር፥ ኔጌብን፥ የተራራውን ቊልቊለትና ነገሥታቱን ሁሉ ያዘ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሁሉንም ፈጀ እንጂ አንድ ሰው እንኳ በሕይወት እንዲኖር አላስተረፈም።


የገባዖን ሰዎችም ሰፈሩን በጌልገላ አድርጎ ወደነበረው ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲሉ መልእክት ላኩበት፦ “በተራራማው አገር የሚኖሩት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ እኛን ሊወጉን ስለ ተባበሩብን እኛ አገልጋዮችህን ችላ አትበል! በቶሎ ወደ እኛ ወጥተህ እርዳንና አድነን!”


ነገር ግን ሦስት ቀን ተኩል ካለፈ በኋላ ሕይወት የሚሰጥ እስትንፋስ ከእግዚአብሔር መጥቶ ወደ ሬሳዎቹ ገባ፤ በእግራቸውም ቆሙ፤ ያዩአቸውም ሰዎች እጅግ ፈሩ።


跟着我们:

广告


广告