Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 4:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ኃጢአት መሥራቱን እንዳወቀ ወዲያውኑ ምንም ነውር የሌለባት እንስት ፍየል ለኃጢአት መሥዋዕት ያቅርብ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ኀጢአት መሥራቱን በተረዳ ጊዜ፣ እንከን የሌለባትን እንስት ፍየል ስለ ፈጸመው ኀጢአት የግሉ መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ለእርሱም የሠራው ኃጢአት የታወቀ ቢሆን፥ ስለ ሠራው ኃጢአት ነውር የሌለባትን እንስት ፍየል ለቁርባኑ ያመጣል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ለእ​ር​ሱም የሠ​ራው ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቀ​ውና ንስሓ ቢገባ፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት ነውር የሌ​ለ​ባ​ትን እን​ስት ፍየል ለቍ​ር​ባኑ ያመ​ጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ለእርሱም የሠራው ኃጢአት ቢታወቀው፥ ስለ ሠራው ኃጢአት ነውር የሌለባትን እንስት ፍየል ለቍርባኑ ያመጣል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 4:28
12 交叉引用  

በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”


ኃጢአታችንን በፊትህ ታኖራለህ፤ የተሰወረውንም በደላችንን ለአንተ በሚታይ ቦታ ታስቀምጣለህ።


እንግዲህ እግዚአብሔር ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ‘ዐማኑኤል’ ብላ ትጠራዋለች፤


እናንተ እምነት የጐደላችሁ ሕዝብ፥ እስከ መቼ ታመነታላችሁ? እኔ እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገርን ፈጥሬአለሁ፤ ይኸውም ሴት ለወንድ ትከላከላለች። ልዩ የሆነ አዲስ ነገር ፈጥሬአለሁ።”


የተሠራው ኃጢአት እንደ ታወቀ ወዲያውኑ ማኅበሩ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት የሚሆን አንድ ወይፈን ያምጣ፤ እርሱንም ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ያቅርቡት፤


ኃጢአት መሥራቱን እንዳወቀ ወዲያውኑ ምንም ነውር የሌለበትን ተባዕት ፍየል የኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርጎ ያምጣ።


“ተቀብቶ የተሾመው ካህን ኃጢአት ሠርቶ ሕዝቡን እንደ በደለኛ የሚያስቈጥር ሆኖ ቢገኝ፥ ምንም ነውር የሌለበትን አንድ ወይፈን ያምጣ፤ ስለ ኃጢአቱም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ ያቅርበው።


“ሰውየው ስለ ኃጢአቱ ስርየት የበግ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥ ምንም ነውር የሌለባት እንስት ትሁን።


ስለ ሠራው ኃጢአት ለእግዚአብሔር የበደል መሥዋዕት ያምጣ፤ ይኸውም ከመንጋው የበግ ወይም የፍየል እንስት ይሆናል፤ ካህኑም ስለ ኃጢአቱ ያስተሰርይለታል።


ከሰው ባሕርይ ደካማነት የተነሣ ሕግ ሊያደርገው ያልቻለውን እግዚአብሔር አድርጎታል፤ የገዛ ልጁንም በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌነት በኃጢአት ምክንያት ልኮ በሥጋው ኃጢአትን በፍርድ አስወገደ።


ሁላችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ስለ ሆናችሁ በአይሁዳዊና በግሪካዊ፥ በአገልጋይና በጌታ፥ በወንድና በሴት መካከል ምንም ልዩነት የለም።


跟着我们:

广告


广告