Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 4:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “ኃጢአት የሠራውና ባለማወቅ እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዘው ትእዛዝ በመተላለፍ በደለኛ የሆነው የሕዝብ መሪ ከሆነ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ ‘አንድ የሕዝብ መሪ ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፣ አምላኩም እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ከከለከላቸው ትእዛዞች አንዱን ተላልፎ ቢገኝ፣ እርሱ በደለኛ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “አንድ ገዢም ኃጢአትን ቢሠራ፥ ጌታም አምላኩ አትሥራ ያለውን ትእዛዝ አንዱን ባለማወቅ ሠርቶ ቢበድል፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “መኰ​ን​ንም ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ሳያ​ው​ቅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኩ፦ አት​ሥራ ያለ​ውን ትእ​ዛዝ ቢተ​ላ​ለፍ፥ እን​ዲ​ህም ቢበ​ድል፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አንድ መኰንንም ኃጢአትን ሲሠራ፥ ሳያውቅም እግዚአብሔር አምላኩ፦ አትሥራ ያለውን ትእዛዝ ሲተላለፍ፥ እንዲህም ሲበድል፥

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 4:22
15 交叉引用  

ኃጢአት እንዳይሠለጥንብኝ ዐውቆ ከመበደል ጠብቀኝ፤ ይህም ከሆነ ታላቅ በደል ከመሥራት ንጹሕ እሆናለሁ።


በተጨማሪ ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መርጠህ በሕዝቡ ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርገህ ሹም። እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥ እምነት የሚጣልባቸውና በጉቦም የማይደለሉ ሰዎች መሆን አለባቸው።


ወደ ኃጢአት እንዳይመራህ ለአንደበትህ ከገደብ ያለፈ ነጻነት አትስጠው፤ በዚህ ዐይነት “ይህን የተናገርኩት ሳላውቅ ነው” ብለህ በእግዚአብሔር አገልጋይ ፊት ይቅርታ ከመጠየቅ ትድናለህ፤ አለበለዚያ ግን የደከምክበትን ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቊጣ በገዛ እጅህ እንደ መጋበዝ ይሆንብሃል።


“ባለማወቅ ኃጢአት የሠራው መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ቢሆንና፥ ጉዳዩም ከማኅበረሰቡ ቢሰወር፥ ይህም ኃጢአት እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ትእዛዞች አንዱን በማፍረስ በደለኞች ቢያደርጋቸው፥


“ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ማንም ሰው ተሳስቶ ኃጢአት ቢሠራ ወይም ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዱን ቢተላለፍ ከዚህ የሚከተለውን ሥርዓት ይጠብቅ፦


“ኃጢአት የሠራውና ባለማወቅም እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ትእዛዞች አንዱን የተላለፈውና በደለኛ የሆነው ሰው ከተራው ሕዝብ ወገን ከሆነ፥


“አንድ ሰው ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዲቱን ቢተላለፍ በደለኛ ይሆናል።


“ምናልባት እናንተ ሆን ብላችሁ ሳይሆን ባለማወቅ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ትእዛዞች መካከል አንዱን ሳትጠብቁ ብትቀሩ፥


እንዲህ ዐይነቱ ስሕተት የተፈጸመው በማኅበሩ አለማወቅ ከሆነ አንድ ወይፈን አምጥተው መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት፤ ከእርሱም ጋር ተገቢውን የእህልና የወይን ጠጅ ቊርባን ያቅርቡ፤ በተጨማሪም አንድ ተባዕት ፍየል ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ።


ከእነርሱም ጋር በእስራኤላውያን ዘንድ ዝናቸው የታወቀና ለሕዝብ መሪነት የተመረጡ ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎችን ወስደው በሙሴ ላይ ተነሡ፤


ሙሴ፥ አልዓዛርና ሌሎቹም የማኅበሩ መሪዎች ሠራዊቱን ለመቀበል ከሰፈር ወጡ፤


ወደ ሙሴና አልዓዛር እንዲሁም ወደ ሌሎቹ የማኅበሩ መሪዎች ሄደው እንዲህ አሉ፤


አንድ ሰው ባለማወቅ ተሳስቶ ሰው ቢገድል አምልጦ የሚደበቅበት የመማጠኛ ከተሞችን ምረጥ።


跟着我们:

广告


广告