Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 3:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ኲላሊቶቹና በእነርሱ ላይ የሚገኘው ስብ፥ እንዲሁም እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን ከሚሸፍነው ስብ ምርጥ የሆነው ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሁለቱን ኵላሊቶች፣ በኵላሊቶቹ ላይና በጐድኑ አጠገብ ያለውን ሥብ እንዲሁም የጕበቱን መሸፈኛ፣ ከኵላሊቶቹ ጋራ አንድ ላይ አውጥቶ ያቅርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሁለቱንም ኩላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኩላሊቶች ጋር ወስዶ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይና በጎ​ድኑ አጠ​ገብ ያለ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ ከኵ​ላ​ሊ​ቶቹ ጋር ያመ​ጣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጕበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኵላሊቶች ጋር ይወስዳል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 3:4
15 交叉引用  

ከዚህ በኋላ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሞራ እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን የሚሸፍነውን ሞራ ሁለቱን ኲላሊቶቹንና እነርሱን የሚሸፍነውን ሞራ ወስደህ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው።


“የሚካኑበት ስለ ሆነ የአውራውን በግ ሞራ ላቱን፥ የውስጥ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሞራ፥ እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን ከሚሸፍነው ሞራ የተሻለውን ክፍል፥ ሁለቱን ኲላሊቶቹን፥ እነርሱን የሚሸፍነውን ሞራና በቀኝ በኩል ያለውን የኋላ እግር ቈርጠህ ለያቸው።


ያም ሰው እንስሳውን በየብልቱ ከቈራረጠው በኋላ ካህኑ ብልቶቹን ሁሉ፥ ራሱንና ስቡን ጭምር በመሠዊያ ላይ ተረብርቦ በሚቃጠለው እንጨት ላይ ያኑር፤


የእንስሳውንም ሥጋ ብልቶች በየዐይነታቸው ለያይተው ራሱንና ስቡንም ጭምር በመሠዊያው ላይ በተረበረበው እንጨት ላይ ያኑሩት።


ኲላሊቶቹና እነርሱ የተሸፈኑበት ስብ፥ እንዲሁም እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን የሚሸፍነው ምርጥ ስብ ናቸው።


ኲላሊቶቹንና እነርሱ የተሸፈኑበትን ስብ፥ እንዲሁም እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱ ከተሸፈነበት ስብ ምርጥ የሆነውን ወስደው፥


ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው መባ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡት ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነው ስብ በሙሉ፥


ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በመሆኑ የአሮን ልጆች በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠዊያ ላይ ያቃጥሉት፤ ይህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው።


ከዚህም ኰርማ ስቡን ሁሉ፥


ኲላሊቶቹን፥ እነርሱም የተሸፈኑበትን ስብና እንዲሁም እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን ከሸፈነው ስብ ምርጥ የሆነውን ይውሰድ።


ኲላሊቶቹና በእነርሱ ላይ የሚገኘው ስብ፥ እንዲሁም እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን ከሚሸፍነው ስብ ምርጥ የሆነው ክፍል ተወስዶ በመሠዊያው ላይ መሥዋዕት ሆኖ ይቅረብ፤


ሙሴ በእንስሳው ሆድ ዕቃ ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ ጒበቱን እንደ መረብ ሆኖ የሚሸፍነው ስብ፥ ኲላሊቶቹንና በእነርሱ ላይ ያለውን ስብ ወስዶ፥ ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠለው።


ስቡን፥ ላቱን፥ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ እንደ መረብ ሆኖ ጒበቱን ከሚሸፍነው ስብ ምርጥ የሆነውን ክፍል፥ ኲላሊቶቹን፥ በእነርሱ ላይ ያለውን ስብና በቀኝ በኩል ያለውን ወርች ወሰደ፤


ከዚህም በኋላ ስቡን፥ ኲላሊቶቹን እንደ መረብ ሆኖ ጒበቱን ከሚሸፍነው ስብ ምርጥ የሆነውን ወስዶ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመሠዊያው ላይ አቃጠለው፤


አሮንም የወይፈኑንና የበግ አውራውን ስብ ሁሉ ማለትም ላቱን፥ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ እንደ መረብ ሆኖ ጒበቱን የሚሸፍነውን ስብ ምርጥ የሆነውን ክፍል፥ ኲላሊቶቹንና በእነርሱ ላይ ያለውን ስብ ወስዶ፥


跟着我们:

广告


广告