ዘሌዋውያን 27:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 ባለ ንብረቱ እንስሶቹ በየዐይነቱ በሚመድብበት ጊዜ ነውረኛውን ከደኅነኛው አይለይ፤ በእርሱም ሌላ ምትክ አያድርግ። በአንዱ እንስሳ ሌላ እንስሳ ተክቶ ቢገኝ ግን፥ ሁለቱም እንስሶች ለእግዚአብሔር የተለዩ ይሁኑ፤ እንደገና መዋጀትም የለባቸውም።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም33 ሰውየው መልካም የሆነውን መልካም ካልሆነው አይለይ ወይም አይተካ፤ አንዱን በሌላው ቢተካ ግን ሁለቱም እንስሳት የተቀደሱ ይሆናሉ፤ ሊዋጁም አይችሉም።’ ” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 መልካም ወይም መጥፎ እንደሆነ አይመርምር፥ አይለውጥም፤ ቢለውጠውም እርሱና ልዋጩ ሁለቱም የተቀደሱ ይሆናሉ፤ አይቤዥም።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 መልካሙን በክፉ፥ ክፉውንም በመልካም አይለውጥ፤ ቢለውጠውም እርሱና ልዋጩ የተቀደሱ ይሆናሉ፤ አይቤዠውም።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 መልካም ወይም ክፉ እንዲሆን አይመርምር፥ አይለውጥም፤ ቢለውጠውም እርሱና ልዋጩ የተቀደሱ ይሆናሉ፤ አይቤዠውም። 参见章节 |