ዘሌዋውያን 26:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም41 እነርሱን ተቃውሜ ወደ ጠላቶቻቸው አገር እንዲሰደዱ አደረግሁ፤ ሆኖም እልኸኛ ልባቸው በትሕትና ተሰብሮ ከኃጢአታቸው ቢታረሙ፥ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም41 ይኸውም፣ እኔ ጠላት እንድሆንባቸውና ወደ ጠላቶቻቸው ምድር እንድሰድዳቸው ያደረገኝን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድና ስለ ኀጢአታቸው የሚገባውን ቅጣት ቢቀበሉ፣ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)41 እኔም ደግሞ እነርሱን በመቃወም እሄዳለሁ፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የበደላቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)41 እኔም ደግሞ አግድሜ ከእነርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠላቶቻቸውም ምድር አጠፋቸዋለሁ። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ያፍራል፤ ስለ ኀጢአታቸውም ይናዘዛሉ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)41 እኔም ደግሞ በእንቢተኝነት ሄድሁባቸው፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አገባኋቸው፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የኃጢአታቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥ 参见章节 |