Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 25:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 እነርሱንም በውርስ ለልጆቻችሁ ማስተላለፍ ትችላላችሁ፤ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አገልጋዮቻችሁ ይሆናሉ፤ ከእስራኤላውያን ወገኖቻችሁ መካከል ግን ማንንም በማስጨነቅ አትግዙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 እነርሱንም እንደ ንብረት ለልጆቻችሁ አውርሷቸው፤ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ባሪያዎች ይሁኗችሁ፤ እስራኤላውያን ወገኖቻችሁን ግን በጭካኔ አትግዟቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁ ለዘለዓለም እንዲወርሱአቸው ተዉአቸው፤ እነርሱን ባርያዎች ታደርጋላችሁ፥ ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ወንድሞቻችሁ ናቸውና አንዱ ሌላውን በጽኑ እጅ አይግዛው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ታወ​ር​ሱ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱም ለእ​ና​ንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ውርስ ይሆ​ናሉ፤ ነገር ግን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማና​ቸ​ውም ሰው ወን​ድ​ሙን በሥራ አያ​ስ​ጨ​ን​ቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁ ይወርሱአቸው ዘንድ ተዉአቸው፤ ከእነርሱም ባሪያዎችን ለዘላለም ትወስዳላችሁ፤ ነገር ግን የእስራኤልን ልጆች ወንድሞቻችሁን በጽኑ እጅ አትግዙአቸው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 25:46
5 交叉引用  

ርኅራኄ በጐደለውም ጭካኔ በባርነት አሠሩአቸው።


የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል።


እነርሱን በማስጨነቅ አትግዛቸው፤ ነገር ግን እኔን አምላክህን ፍራ።


እንዲሁም በመካከላችሁ የሚኖሩትን የመጻተኞችን ልጆች መግዛት ትችላላችሁ፤ በምድራችሁ የተወለዱትም እንደነዚህ ያሉት ልጆች የራሳችሁ ንብረት መሆን ይችላሉ።


“ምናልባት በመካከልህ የሚኖር አንድ መጻተኛ ባለጸጋ ሲሆን፥ እስራኤላዊ ወገንህ ደኽይቶ ለዚያ መጻተኛ ወይም ከእርሱ ቤተሰብ ለአንዱ ራሱን በባርነት ያስገዛ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告