Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 25:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ይህንንም ማድረግ በሚችልበት ጊዜ እስከ ተከታዩ የንብረት መመለስ ዓመት ያለውን ዘመን ቈጥሮ ቀሪውን ገንዘብ ለገዛው ሰው ከመለሰለት በኋላ ወደ ርስቱ ይመለስ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ርስቱን ከሸጠበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን የሽያጭ ዘመን በመቍጠር የዋጋውን ልዩነት ለገዛው ሰው ይመልስ፤ እርሱም ወደ ገዛ ርስቱ ይመለስ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እርሱም እስከ ሸጠበት ጊዜ ያሉትን ዓመታት ያሰላል፥ ከዚያም የቀረውን ወደ ገዛው ሰው ይመልሳል፤ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የሽ​ያ​ጩን ዘመን ቈጥሮ የቀ​ረ​ውን ወደ ገዛው ሰው ይመ​ልስ፤ እር​ሱም ወደ ርስቱ ይመ​ለስ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የሽያጩን ዘመን ቈጥሮ የቀረውን ወደ ገዛው ሰው ይመልስ፤ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለስ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 25:27
5 交叉引用  

ዓመታቱ ብዙ ቢሆኑ፥ ዋጋው ከፍ ይላል፤ ዓመታቱ ጥቂቶች ከሆኑ ዋጋው ዝቅ ይላል፤ የሚሸጥበት ዋጋ የሚተመነው ምድሪቱ በምታስገኘው ሰብል መጠን ነው፤


“መሬት በሚሸጥበት ጊዜ የቀድሞ ባለቤቱ መልሶ ለመዋጀት መብት ያለው መሆኑ መታወቅ አለበት።


ሊዋጅለት የሚችል የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ግን ዘግየት ብሎ ሀብት በሚያገኝበት ጊዜ እርሱ ራሱ መዋጀት ይችላል።


አጐቱ፥ የአጐቱ ልጅ ወይም ከቅርብ ዘመዶቹ አንዱ መልሶ ሊዋጀው ይችላል፤ በቂ ገንዘብ ካጠራቀመም የራሱን ነጻነት ራሱ መዋጀት ይችላል።


መሬቱን የሰጠው የኢዮቤልዩ ዓመት ካለፈ ዘግይቶ ከሆነ ግን ካህኑ እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ያለውን ቀሪ ጊዜ በመገመት ዋጋው እንዲቀነስ ያድርግ።


跟着我们:

广告


广告