Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 23:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እስከ ሰባት ቀን ድረስ የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ የዕለት ተግባራችሁን ማከናወን ትታችሁ በሰባተኛው ቀን ለአምልኮ ትሰበሰባላችሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሰባት ቀን በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ በዚያ ዕለት የተለመደ ተግባራችሁን አታከናውኑ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሰባት ቀንም ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን አቅርቡ፤ በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ነው፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሰባት ቀንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ፤ ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ቅድ​ስት ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን አቅርቡ፤ በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ነው፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 23:8
9 交叉引用  

ከዚያም ሰባት ቀኖች በመጀመሪያውና በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፤ በነዚያም ቀኖች ምግባችሁን ከማዘጋጀት በቀር ምንም ሥራ አትሠሩም።


ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ የሌለበት ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር ክብር በዓል ታደርጋላችሁ።


በዓሉ በሚከበርባቸው ሰባት ዕለቶች በእያንዳንዱ ቀን ምንም ነውር የሌለባቸውን ሰባት ኰርማዎችና ሰባት የበግ አውራዎች በሙሉ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን ያዘጋጃል፤ ከዚህም ጋር በእያንዳንዱ ዕለት ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን አንድ የፍየል አውራ ያዘጋጃል።


ከእነዚህ ዕለቶች በመጀመሪያው ቀን ለአምልኮ ትሰበሰባላችሁ፤ ከዕለት ተግባራችሁ ማንኛውንም በዚህ ቀን አትሠሩም።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦


በበዓሉ መጀመሪያ ቀን ለአምልኮ ትሰበሰባላችሁ፤ በእርሱ ምንም ሥራ አትሠሩበትም።


በሰባተኛው ቀን ለአምልኮ ትሰበሰባላችሁ፤ በእርሱ ምንም ሥራ አትሠሩም።


“በመከር በዓል መጀመሪያ ቀን አዲስ እህል ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ በምታቀርቡበት ጊዜ ለአምልኮ ትሰበሰባላችሁ፤ ሥራም አትሠሩም፤


በሚከተሉት ስድስት ቀኖች ደግሞ እርሾ ሳይነካው የተዘጋጀ ቂጣ ትበላለህ፤ በሰባተኛው ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ትሰግድ ዘንድ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት።


跟着我们:

广告


广告