Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 23:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ስለዚህም እኔ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ምድር ባወጣሁ ጊዜ ዳሶችን እየጣሉ እንዲኖሩ ማድረጌን የልጅ ልጆቻችሁ ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 በዚህም እኔ እስራኤላውያንን ከግብጽ ባወጣሁ ጊዜ፣ ዳስ ውስጥ እንዲቀመጡ ማድረጌን የልጅ ልጆቻችሁ ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 በዚህም ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በዳሶች ውስጥ እንዳስቀመጥኋቸው የልጅ ልጆቻችሁ እንዲያውቁ ነው፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ከግ​ብፅ ምድር ባወ​ጣ​ኋ​ቸው ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በዳስ ውስጥ እን​ዳ​ስ​ቀ​መ​ጥ​ኋ​ቸው የልጅ ልጆ​ቻ​ችሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ያሉት የሀ​ገር ልጆች ሁሉ በዳስ ውስጥ ይቀ​መጡ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 23:43
6 交叉引用  

አራት መቶ ሠላሳው ዓመት በተፈጸመበትም ቀን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ የግብጽን ምድር ለቆ ወጣ።


በዚያን ቀን እግዚአብሔር መላውን የእስራኤል ሕዝብ በክፍል በክፍል ከግብጽ ምድር መርቶ አወጣ።


በሚመጡት ዘመናት ልጆችህ የዚህን ሥርዓት ትርጒም ቢጠይቁህ፥ እንዲህ በማለት ታስረዳቸዋለህ፦ ‘በባርነት ከተገዛንበት ከግብጽ ምድር እግዚአብሔር በታላቅ ኀይል አወጣን፤


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ በዚህ በሰባተኛው ወር ከዐሥራ አምስተኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የዳስ በዓል ይከበራል።


跟着我们:

广告


广告