ዘሌዋውያን 23:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ካህኑም ከበኲራቱ እንጀራ ከሁለቱ ጠቦቶች ጋር በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቀርባል፤ እርሱም የካህናቱ ድርሻ ሆኖ ይነሣል፤ እነዚህም ስጦታዎች የተቀደሱ ናቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ካህኑም ሁለቱን የበግ ጠቦቶች ከበኵራቱ እንጀራ ጋራ የሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ እነዚህም ለእግዚአብሔር ቅዱስ መሥዋዕት፣ የካህኑም ድርሻ ናቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ካህኑም ከበኩራቱ እንጀራ ከሁለቱም ጠቦቶች ጋር በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ይወዘውዛቸዋል። ለካህኑ ለጌታ የተቀደሱ ይሆናሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ካህኑም ከበኵራቱ ኅብስት፥ ከሁለቱም ጠቦቶች ጋር በእግዚአብሔር ፊት ለቍርባን ያቅርበው፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ፈንታ ነው፤ ላቀረበው ለካህኑ ይሁን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ካህኑም ከበኵራቱ እንጀራ ከሁለቱም ጠቦቶች ጋር በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን ይወዘውዛቸዋል፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ፈንታ ነው፤ ለካህኑ ይሁን። 参见章节 |