Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 23:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ይህንንም ስጦታ ለእግዚአብሔር ከማቅረባችሁ በፊት ከአዲሱ እህል ጥሬውን ወይም የተቈላውን ወይም እንጀራ ጋግራችሁ አትብሉ። ይህም ድንጋጌ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በልጅ ልጆቻችሁ ተጠብቆ ይኑር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስጦታውን ለአምላካችሁ እስከምታቀርቡበት እስከዚያ ቀን ድረስ፣ እንጀራም ቢሆን ቈሎ ወይም እሸት አትብሉ፤ ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለሚመጡት ትውልዶች የዘላለም ሥርዐት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የአምላካችሁን ቁርባን እስከምታመጡበት እስከዚህ ቀን ድረስ እንጀራውንም፥ የተጠበሰውንም እሸት፥ ለምለሙንም እሸት አትብሉ። ይህ በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እን​ጀ​ራ​ው​ንም፥ የተ​ጠ​በ​ሰ​ው​ንም እሸት፥ ለም​ለ​ሙ​ንም እሸት የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ቍር​ባን እስ​ከ​ም​ታ​ቀ​ር​ቡ​በት እስ​ከ​ዚህ ቀን ድረስ አት​ብሉ። ይህ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​በት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እንጀራውንም፥ የተጠበሰውንም እሸት፥ ለምለሙንም እሸት የአምላካችሁን ቍርባን እስከምታቀርቡበት እስከዚህ ቀን ድረስ አትብሉ። ይህ በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 23:14
15 交叉引用  

የተቀደሰውን ሰንበትህንም እንዲያውቁ አደረግሃቸው፤ በአገልጋይህም በሙሴ አማካይነት ትእዛዞችህን፥ ድንጋጌህንና ሕጎችህን ሰጠሃቸው።


የእግዚአብሔር ሕግ ትክክል ነው፤ ለልብ ደስታን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ ለዐይን ብርሃንን ይሰጣል።


አሮንና ልጆቹ ከምሽት እስከ ንጋት ይበራ ዘንድ የእግዚአብሔር መገኛ ከሆነው ፊት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ካለው መጋረጃ ውጪ ያኑሩት፤ ይህም በእስራኤል ሕዝብና ወደፊትም በሚነሣው ትውልድ ዘንድ ቋሚ ሥርዓት ሆኖ ይኑር።


“በየዓመቱ የመከራችሁን በኲራት ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ። “የበግም ሆነ የፍየል ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅሉ።”


በሙሴ አማካይነት እግዚአብሔር የሰጠውን ድንጋጌ ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ አስተምሩ።”


የመከር ወራት መጀመሪያ የሆነውን በኲራት በምታቀርብበትም ጊዜ ተጠብሶ የታሸ እሸት ይሁን።


ስለዚህ በዚያን ዕለት ምንም ሥራ እንዳትሠሩ፤ ይህም የሥርዓት መመሪያ በምትኖሩበት ቦታ ሁሉ ለልጅ ልጆቻችሁ ተጠብቆ ይኖራል።


ይህንንም በዓል በየዓመቱ በሰባተኛው ወር ለሰባት ቀን ለእግዚአብሔር በደስታ አክብሩ፤ ይህም ለልጅ ልጆቻችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው፤


ከእስራኤላውያን ወገን ስብ የሆነውን ሥጋ ወይም የእንስሶችን ደም የሚመገብ አይኑር፤ ይህም እስራኤላውያን በሚኖሩበት ዘመንና ቦታ ሁሉ ለዘለዓለሙ ተጠብቆ የሚኖር ቋሚ ሥርዓት ይሁን።


እነዚህን ድንጋጌዎች በጥንቃቄ ጠብቅ፤ አንተም ቀድሞ በግብጽ ባሪያ እንደ ነበርክ አስታውስ።


跟着我们:

广告


广告