Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 20:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አንድ ሰው የአባቱ ሚስት ከሆነችው ሴት ጋር ቢተኛ፥ የአባቱን ኀፍረተ ሥጋ ስለ ገለጠ እርሱና ሴትዮዋ ሁለቱም በሞት ይቀጡ፤ የተፈረደባቸውም በራሳቸው በደል ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ ‘አንድ ሰው ከአባቱ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም አባቱን አዋርዷል፤ ሰውየውና ሴትዮዋ ይገደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ማናቸውም ሰው ከአባቱ ሚስት ጋር ቢተኛ የአባቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ሁለቱ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ማና​ቸ​ውም ሰው ከአ​ባቱ ሚስት ጋር ቢተኛ የአ​ባ​ቱን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገል​ጦ​አል፤ ሁለ​ቱም ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ማናቸውም ሰው ከአባቱ ሚስት ጋር ቢተኛ የአባቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ሁለቱ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 20:11
7 交叉引用  

“ማንም ሰው ፍትወታዊ ግንኙነት ለማድረግ ወደ ሥጋ ዘመዱ አይቅረብ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤


ደካሞችንና ረዳት የሌላቸውን በትቢያ ላይ ጥለው ራስ ራሳቸውን ይረግጣሉ፤ የተዋረዱ ምስኪኖችንም ገፍትረው ከመንገድ ያስወጣሉ፤ አባትና ልጅ ሁለቱም ከአንዲት ሴት ጋር ያመነዝራሉ፤ በዚህም ሥራቸው የተቀደሰውን ስሜን ያረክሳሉ።


በመካከላችሁ አሳፋሪ የዝሙት ሥራ መኖሩ ይወራል፤ እንዲህ ዐይነቱ የዝሙት ሥራ በአሕዛብ ዘንድ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የእንጀራ እናቱን እንደ ሚስት አድርጎ የሚኖር አለ ተብሎአል።


“ማንም ሰው የአባቱ ሚስት ከሆነችው ከማንኛይቱም ሴት ጋር ግንኙነት በማድረግ አባቱን አያሳፍር።


“ ‘የአባቱ ሚስቶች ከሆኑት ከየትኛዋም ጋር ግንኙነት በማድረግ የአባቱን ክብር የሚያዋርድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።


“ ‘ከዐማቱ ጋር ግንኙነት የሚፈጽም ወንድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።


跟着我们:

广告


广告