Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 19:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ትክክለኞች የሆኑ ሚዛኖች ማለት የርዝመት፥ የክብደትና የፈሳሽ መለኪያዎች ይኑሩአችሁ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 የጽድቅ መለኪያ፣ የጽድቅ ሚዛን፣ የጽድቅ የኢፍ መስፈሪያ፣ የጽድቅ የሂን መስፈሪያም ይኑራችሁ። ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ትክክለኛም ሚዛን፥ ትክክለኛም መመዘኛ፥ ትክክለኛም የኢፍ መስፈሪያ፥ ትክክለኛም የኢን መስፈሪያ ይኑሩአችሁ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 የእ​ው​ነ​ትም ሚዛን፥ የእ​ው​ነ​ትም መመ​ዘኛ፥ የእ​ው​ነ​ትም የፈ​ሳሽ መስ​ፈ​ሪያ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እኔ ነኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 የእውነትም ሚዛን፥ የእውነትም መመዘኛ፥ የእውነትም የኢፍ መስፈሪያ፥ የእውነትም የኢን መስፈሪያ ይሁንላችሁ፤ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ ነኝ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 19:36
11 交叉引用  

ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ለሚቀርበው ኅብስትና ዱቄት፥ ያለ እርሾ ለሚጋገረው ቂጣና በወይራ ዘይት ለሚለወሰው ዱቄት ኀላፊዎች ሲሆኑ፥ ለቤተ መቅደስ መባ ሆኖ የሚቀርበውን ሁሉ የሚመዝኑና የሚለኩ እነርሱ ነበሩ፤


“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በባርነት ከምትኖርባት ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤


እግዚአብሔር በሐሰተኛ ሚዛን የሚያታልሉትን ሰዎች ይጠላል፤ በትክክለኛ ሚዛን በሚመዝኑት ሰዎች ግን ይደሰታል።


ሚዛንና መስፈሪያ ትክክል እንዲሆኑ፥ ለሽያጭ የሚቀርቡት ዕቃዎች ሁሉ ሚዛናቸው የተስተካከለ እንዲሆን የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነው።


እግዚአብሔር በሐሰተኛ ሚዛንና ትክክል ባልሆነ መስፈሪያ የሚጠቀሙ ሰዎችን ይጠላል።


“እያንዳንዱ ሰው ትክክለኛ ሚዛንና መለኪያ እንዲሁም እኩል የሆነ መስፈሪያ ይኑረው።


አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር መርቼ ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስለዚህም እኔ ቅዱስ ስለ ሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።


ለሰጠኋችሁ ሕግና ትእዛዝ ሁሉ ታማኞች ሁኑ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


ታዲያ በሐሰተኛ ሚዛንና መስፈሪያ የሚጠቀሙትን ሰዎች እታገሣለሁን?


እኔም “ይህ ነገር ምንድን ነው?” አልኩት። እርሱም “በምድሪቱ ሁሉ ላይ የሚሠራውን ኃጢአት የሚያመለክት ቅርጫት ነው” አለኝ።


跟着我们:

广告


广告