Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 19:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ካህኑም የዚያን ሰው ኃጢአት በአውራ በጉ የበደል መሥዋዕት ያስተሰርይለታል፤ እኔ እግዚአብሔርም በደሉን ይቅር እለዋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ካህኑም በበደል መሥዋዕቱ አውራ በግ፣ ሰውየው ስለ ሠራው ኀጢአት በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት በጌታ ፊት የበደል መሥዋዕት በሆነው በግ ለእርሱ ያስተሰርይለታል፥ የሠራውም ኃጢአት ይቅር ይባላል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ካህ​ኑም ስለ ሠራው ኀጢ​አት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት በግ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ የሠ​ራ​ውም ኀጢ​አት ይቀ​ር​ለ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት በበደል መሥዋዕት በግ ያስተሰርይለታል የሠራውም ኃጢአት ይቀርለታል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 19:22
7 交叉引用  

ይህን በደል የፈጸመ ሰው ለበደል ስርየት መሥዋዕት አድርጎ አንድ የበግ አውራ ወደ መገናኛው ድንኳን ወደ እኔ ያምጣ።


“ወደ ከነዓን ምድር ገብታችሁ ማንኛውንም ፍሬ የሚሰጥ ዛፍ በምትተክሉበት ጊዜ እስከ መጀመሪያው ሦስት ዓመት ድረስ የሚሰጠውን ፍሬ መብላት የተከለከለ መሆኑን አስታውሱ። በእነዚህም ዓመቶች ውስጥ ፍሬው አይበላም።


አፈጻጸሙም ለኃጢአት መሥዋዕት በሚቀርበው ኰርማ ላይ በሚደረገው ዐይነት ይሁን፤ በዚህም ዐይነት ስለ ሕዝቡ ኃጢአት መሥዋዕትን ያቀርባል፤ ሕዝቡም የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ።


ስቡንም ሁሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ የዚህም አፈጻጸም ለአንድነት መሥዋዕት የቀረቡትን እንስሶች ስብ ባቃጠለው ዐይነት ይሁን፤ በዚህም ዐይነት ካህኑ ስለ ሕዝቡ መሪ ኃጢአት መሥዋዕት በማቅረብ ያስተሰርያል፤ መሪውም የኃጢአቱን ይቅርታ ያገኛል።


ለአንድነት መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶችን ስብ በመግፈፍ በሚፈጽመው ዐይነት የዚህችንም እንስሳ ስብ ሁሉ ገፎ ያስወግድ፤ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በዚህ ዐይነት ካህኑ ስለዚያ ሰው የኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ያቀርባል፤ ያም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።


ከዚህም በኋላ ለአንድነት መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶችን ስብ በመግፈፍ በሚፈጽመው ዐይነት የዚህችንም እንስሳ ስብ ሁሉ ገፎ ያስወግድ፤ እርሱንም ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው የምግብ መባ ጋር በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በዚህም ዐይነት ካህኑ ስለዚያ ሰው የኃጢአት መሥዋዕትን በማቅረብ ያስተስርይለት፤ ያም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።


“አንድ ሰው በግ ወይም ፍየል ማቅረብ ካልቻለ ግን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንደኛይቱን ስለ ኀጢአት ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሁለተኛይቱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ የበደሉን ዕዳ ይከፍል ዘንድ ለእግዚአብሔር ያምጣ።


跟着我们:

广告


广告