Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 17:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከእስራኤል ሕዝብ ማናቸውም ሰው በሬ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈሩ ውጪ ቢያርድ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ማንኛውም እስራኤላዊ በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈር ውጭ በሬ፣ በግ ወይም ፍየል ቢያርድ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከእስራኤል ቤት ማናችውም ሰው በሬ ወይም በግ ወይም ፍየል በሰፈሩ ውስጥ ቢያርድ፥ ወይም ከሰፈሩ ውጭ ቢያርደው፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው በሬ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ቢያ​ርድ፥ በሰ​ፈሩ ውስጥ ወይም ከሰ​ፈሩ ውጭ ቢያ​ር​ደው፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከእስራኤል ቤት ማናችውም ሰው በሬ ወይም በግ ወይም ፍየል ቢያርድ፥ በሰፈሩ ውስጥ ወይም ከሰፈሩ ውጭ ቢያርደው፥

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 17:3
11 交叉引用  

በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደሱ ገና አልተሠራም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ በየኮረብታው መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር።


“ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም የውጪ አገር ተወላጅ የሆነ ሰው፥ ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የገደለውን የእንስሳ ሥጋ ቢበላ ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱንም ታጥቦ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል፤


“ ‘እግዚአብሔር ያዘዘው ትእዛዝ ይህ ነው’ ብለህ ለአሮንና ለልጆቹ እንዲሁም ለእስራኤላውያን ሁሉ ንገር፤


በተቀደሰው ስፍራ ለእግዚአብሔር ቊርባን ያቀርብ ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ ደም በከንቱ እንዳፈሰሰ ተቈጥሮ ይፈረድበታል፤ ከሕዝቡም ይለያል።


“ለእነርሱም እንዲህ በላቸው፦ ‘ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በማኅበሩ መካከል የሚኖር መጻተኛ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት ቢያቀርብ፥


መሥዋዕት አቅራቢው ሰው መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ይረደው፤ የአሮን ዘር የሆኑ ካህናትም ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ዙሪያ ይርጩት።


跟着我们:

广告


广告