Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 17:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ገላውን ባይታጠብና ልብሱን ባያጥብ ግን በኃጢአቱ ቅጣቱን ያገኛል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ልብሱን ባያጥብ፣ ሰውነቱንም ባይታጠብ ግን ኀጢአት ሠርቷልና ይጠየቅበታል።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ነገር ግን ልብሱን ባያጥብ፥ ገላውንም ባይታጠብ ኃጢአቱን ይሸከማል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ልብ​ሱ​ንና ገላ​ውን ባያ​ጥብ ግን ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ልብሱንና ገላውን ባያጥብ ግን ኃጢአቱን ይሸከማል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 17:16
11 交叉引用  

ጻድቁ አገልጋዬ ከሥቃዩ በኋላ የሕይወትን ብርሃን አይቶ ይረካል፤ በዕውቀቱም ብዙዎችን ያጸድቃል፤ በደላቸውንም ይሸከማል።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፤


ከእርሱ የሚበላ ማንም ሰው ለእኔ የተቀደሰውን እንደ ተራ ነገር በመቊጠሩ በደል ይሆንበታል፤ ከሕዝቤም ይለያል።


አንድ ሰው እኅቱን ወይም በአንድ በኩል ብቻ ከአባቱ ወይም ከእናቱ የተወለደችውን እኅቱን አግብቶ ፍትወታዊ ግንኙነት ቢያደርጉ ይህ አስነዋሪ ነገር በመሆኑ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ፤ ከእኅቱ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ስላደረገ ፍዳውን ይቀበላል።


“አንድ ሰው በፍርድ አደባባይ በይፋ ለምስክርነት መጥቶ ያየውን ወይም ስለ ጉዳዩ የሚያውቀውን ነገር ባይመሰክር ኃጢአት ይሆንበታል።


ከተረፈው ሥጋ ምንም ያኽል በሦስተኛው ቀን ቢበላ የዚያን ሰው መሥዋዕት እግዚአብሔር አይቀበልለትም፤ መሥዋዕቱም እንደ ቀረበ ሆኖ አይቈጠርለትም፤ እንዲያውም እንደ ረከሰ ሆኖ ይቈጠራል፤ እርሱንም የበላ ሰው የበደሉን ፍዳ ይቀበላል።


ጴጥሮስም “አንተ የእኔን እግር ከቶ አታጥብም!” አለው። ኢየሱስም “እኔ እግርህን ካላጠብኩህ ከእኔ ድርሻ የለህም” አለው።


እንዲሁም ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ አንድ ጊዜ ተሠውቶአል፤ ደግሞም ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን እርሱን የሚጠባበቁትን ለማዳን ሁለተኛ ጊዜ ይገለጣል።


ከኃጢአት ተለይተን በጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።


跟着我们:

广告


广告