Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 16:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆነው የቀረቡትና ኃጢአትን ለማስተስረይ ደማቸው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገብቶ የነበረው ኰርማና ፍየልም ከሰፈር ወደ ውጪ ተወስደው በእሳት ይቃጠሉ፤ እንዲሁም ቆዳቸው፥ ሥጋቸውና የሆድ ዕቃቸው በሙሉ ይቃጠል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ደማቸው ለማስተስረያነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የገባው፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የቀረቡት ወይፈንና ፍየል ከሰፈር ውጭ ተወስደው ቈዳቸው፣ ሥጋቸውና ፈርሳቸው ይቃጠል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ለማስተስረያም እንዲሆን ደማቸው ወደተቀደሰው ስፍራ የገባውን፥ የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈንና የኃጢአቱን መሥዋዕት ፍየል ከሰፈሩ ውጭ ያወጡአቸዋል፤ ቆዳቸውንም፥ ሥጋቸውንም፥ ፈርሳቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ለማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያም እን​ዲ​ሆን ደማ​ቸው ወደ መቅ​ደስ የገ​ባ​ውን የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ቍር​በ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ ሥጋ​ቸ​ው​ንም፥ ፈር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ለማስተስረያም እንዲሆን ደማቸው ወደ መቅደስ የገባውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈንና የኃጢአቱን መሥዋዕት ፍየል ከሰፈሩ ወደ ውጭ ያወጡአቸዋል፤ ቁርበታቸውንም፥ ሥጋቸውንም፥ ፈርሳቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 16:27
8 交叉引用  

ከዚህም በኋላ ኰርማውን ከሰፈር ወደ ውጪ አውጥቶ ስለ ራሱ በደል በቀረበው ወይፈን ላይ እንደተፈጸመው ዐይነት ያቃጥለው፤ ይህም የማኅበረሰቡን ኃጢአት የሚያስወግድ መሥዋዕት ይሆናል።


ከዚያም በኋላ ልብሱን ለውጦ ያን ዐመድ ተሸክሞ ከሰፈር ውጪ ያውጣ፤ ንጹሕ በሆነውም ቦታ ይድፋው።


ካህኑ ከሚያቀርበው የእህል መባ ምንም ሳይበላ ሁሉም መቃጠል አለበት።”


ኃጢአትን ለማስወገድ በሚደረገው ሥርዓት ደሙ ወደ ድንኳኑ ውስጥ የገባ ከሆነ ግን እንስሳው መበላት የለበትም፤ ሁሉም በእሳት ይቃጠል።’


ከኰርማው የቀረውንም ቆዳውን፥ ሥጋውንና አንጀቱን ወስዶ፥ እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት ከሰፈር ውጪ አውጥቶ አቃጠለው።


跟着我们:

广告


广告