Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 15:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “ሴት የወር አበባ በምታይበት ጊዜ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ርኩስ ትሆናለች፤ እርስዋንም የሚነካ ማንም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “ ‘ሴት ጊዜውን እየጠበቀ የሚመጣው የደም መፍሰስ ቢኖርባት፣ የወር አበባዋ ርኩሰት እስከ ሰባት ቀን ይቈያል፤ በዚህ ጊዜ ማንም ሰው ቢነካት እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 “ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት ከሰውነቷም ውስጥ የሚፈስሰው ነገር ደም ቢሆን፥ በወር አበባዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች፤ የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖ​ር​ባት፥ በሥ​ጋ​ዋም ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን፥ በግ​ዳ​ጅዋ ሰባት ቀን ትቀ​መ​ጣ​ለች፤ የሚ​ነ​ካ​ትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት በሥጋዋም ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን፥ በመርገምዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች፤ የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 15:19
10 交叉引用  

“ጽዮን እጆችዋን ትዘረጋለች፤ ነገር ግን ማንም የሚያጽናናት የለም፤ ጐረቤቶቹ ሁሉ የያዕቆብ ዘር ጠላቶች እንዲሆኑ እግዚአብሔር አዟል። ኢየሩሳሌምም በመካከላቸው እንደ ርኩስ ነገር ሆናለች።


“የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ሕዝብ በዚህች አገር ሲኖሩ በከንቱ አኗኗራቸውና በመጥፎ ሥራቸው ሁሉ ምድሪቱን አርክሰዋት ነበር፤ በፊቴም የነበራቸው አካሄድ፥ ሴት በወር አበባዋ ወቅት እንደ ርኩስ ሆና የምትታይበትን ያኽል ነበር።


“ሴት ፀንሳ ወንድ ልጅ ብትወልድ፥ በወር አበባዋ እንደሚሆነው ዐይነት እስከ ሰባት ቀን ድረስ የረከሰች ትሆናለች፤


ከዚያም በኋላ በተጨማሪ ደምዋ እስከሚጠራ እስከ ሠላሳ ሦስት ቀን ድረስ የተቀደሰውን ማናቸውንም ነገር መንካት የለባትም፤ ይህ የመንጻትዋም ጊዜ እስከሚፈጸም ድረስ ወደ ተቀደሰው ድንኳን አትግባ።


በወር አበባዋ ጊዜ የምትቀመጥበትም ሆነ የምትተኛበት ነገር ሁሉ ርኩስ ነው።


አንድ ሰው የወር አበባ ካለባት ሴት ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ቢያደርግ የወር አበባዋን ኀፍረት ገልጠዋል ሁለቱም ከሕዝቡ ተለይተው ይባረሩ።


እንዲሁም በልቡ የሚሳብ፥ የሚያረክስ ነገርን የሚነካ፥ ወይም ርኲሰቱ ምንም ዐይነት ቢሆን የረከሰውን ሰው የሚነካ፤


ክፉ ማሰብ፥ ሰው መግደል፥ ማመንዘር፥ ዝሙት ማድረግ፥ መስረቅ፥ በሐሰት መመስከር የሰውን ስም ማጥፋት፥ ይህ ሁሉ ከሰው ልብ ይወጣል።


ለዐሥራ ሁለት ዓመት ደም እየመታት የምትሠቃይ አንዲት ሴት ነበረች።


跟着我们:

广告


广告