ዘሌዋውያን 15:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ፈሳሽ ያለበት ሰው የተቀመጠበትን ዕቃ ሁሉ የሚነካ እስከ ማታ ድረስ የረከሰ ይሆናል፤ ሰውየው የተቀመጠበትን ማንኛውንም ዕቃ የያዘ ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱንም ታጥቦ፥ እስከ ማታ ድረስ የረከሰ ይሆናል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ከበታቹ ያለውንም ነገር ሁሉ የነካ ማንም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። እነዚህንም ነገሮች የሚያነሣ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 እርሱም ከተቀመጠበት በታች ያለውን ማናቸውንም ነገር የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም እንደነዚህ ያሉ ነገሮችን የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ከበታቹም ያለውን ነገር የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው፤ እነዚህንም ነገሮች የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ በውኃም ይታጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ከበታቹም ያለውን ነገር የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው፤ እነዚህንም ነገሮች የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፥ በውኃም ይታጠብ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው። 参见章节 |