ዘሌዋውያን 14:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ካህኑም የበጉን ጠቦትና የወይራውን ዘይት ተቀብሎ በእግዚአብሔር ፊት የመወዝወዝ መሥዋዕት አድርጎ ያቀርበዋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ካህኑም ለበደል መሥዋዕት የሚሆነውን የበግ ጠቦትና አንድ ሎግ ዘይት ይቀበል፤ የሚወዘወዝ መሥዋዕት በማድረግም በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዛቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ካህኑም የበደሉን መሥዋዕት ጠቦትና ዘይትም ያለበትን የሎግ መስፈሪያ ይወስዳል፤ ካህኑም ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ካህኑም የበደሉን መሥዋዕት የበግ ጠቦት የማሰሮውንም ዘይት ይወስዳል፤ በእግዚአብሔርም ፊት ለቍርባን ያቀርበዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ካህኑም የበደሉን መሥዋዕት ጠቦት የሎግ መስፈሪያውንም ዘይት ይወስዳል፤ ካህኑም ለመወዝወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዛቸዋል። 参见章节 |