Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 13:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ነገር ግን በራ በሆነው ራስ ወይም ግንባር ላይ ወደ ቀይነት ያደላ ነጭ ቊስል ቢታይበት እርሱ የሥጋ ደዌ በሽታ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ነገር ግን በመላጣው ወይም በበራው ላይ ነጣ ያለ ቀይ ቍስል ቢወጣበት፣ ያ ከመላጣው ወይም ከበራው የወጣ ተላላፊ በሽታ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ዳሩ ግን በቡሀነቱ ወይም በራሰ በራነቱ ነጣ ብሎ ቀላ ያለ ደዌ ቢኖርበት፥ እርሱ ከቡሀነቱ ወይም ከራሰ በራነቱ የወጣ የለምጽ ደዌ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 በቡ​ሀ​ነቱ ወይም በራሰ በራ​ነቱ ነጭ፥ ወይም ቀላ ያለ ደዌ ቢኖ​ር​በት፥ እርሱ ከቡ​ሀ​ነቱ ወይም ከራሰ በራ​ነቱ የወጣ ለምጽ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 በቡሀነቱ ወይም በራሰ በራነቱ ነጭ ወይም ቀላ ያለ ደዌ ቢኖርበት፥ እርሱ ከቡሀነቱ ወይም ከራሰ በራነቱ የወጣ ለምጽ ነው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 13:42
5 交叉引用  

ዘግየት ብሎም ቊስሉ ባለበት ቦታ ነጭ እባጭ ወይም ቀላ ያለ ቋቁቻ ዐይነት ቊስል ቢወጣበት ወደ ካህኑ ይሂድ፤


“ማንም ሰው በሰውነቱ ላይ እባጭ ወይም ሽፍታ ወይም ቋቊቻ ቢታይና በገላው ላይ የሥጋ ደዌ ቢመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ከልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት።


አንድ ሰው ከግምባሩና ከዐናቱ ጠጒር ቢመለጥ ራሰ በራ ነው እንጂ ንጹሕ ነው።


ካህኑም መርምሮ በበራ ራሱ ወይም በበራ ግንባሩ ላይ በሰውነት ላይ የሚወጣ የሥጋ ደዌ በሽታ ዐይነት ቀላ ያለ የእባጭ ቊስል ቢያገኝ፥


የሻጋታውን ዐይነት በሚመረምርበት ጊዜ ግድግዳውን እየቦረቦሩ የሚበሉት አረንጓዴ ወይም ቀይ ዐይነት ዝንጒርጒር ምልክቶች ቢታዩበት፥


跟着我们:

广告


广告