Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 11:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ይህን ለእስራኤል ሕዝብ ንገሩ፤ በምድሪቱ ከሚገኙት እንስሶች መብላት የምትችሉት እነዚህን ነው፦

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በሏቸው፤ ‘በየብስ ከሚኖሩ እንስሳት ሁሉ የምትበሏቸው እነዚህ ናቸው፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ በሕይወት ከሚኖሩ ከምድር እንስሶች ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩ​አ​ቸው፦ በም​ድር ካሉት እን​ስ​ሳት ሁሉ የም​ት​በ​ሉ​አ​ቸው እን​ስ​ሳት እነ​ዚህ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በሉአቸው፦ ከምድር እንስሶች ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 11:2
22 交叉引用  

እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፦ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህስ ከቶ አይሁን! እኔ ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የበከተ ወይም አውሬ የገደለው ከብትን ሥጋ የበላሁበት ጊዜ የለም፤ ጸያፍ ምግብም አልበላሁም።”


ዳንኤል ከንጉሡ ምግብ በመመገብና የወይን ጠጁንም በመጠጣት ራሱን ላለማርከስ ወሰነ፤ በዚህም ሐሳብ እንዲስማማለት አሽፈናዝን ለመነው።


እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን እንዲህ አላቸው፤


እንደነዚህ ያሉት እንስሶች በእናንተ ዘንድ የረከሱ ሆነው መቈጠር አለባቸው፤ እነርሱን መብላት ቀርቶ በድናቸውን መንካት እንኳ የለባችሁም።


“ከወፎች ወገን ልትጸየፏቸው የሚገባና የማይበሉ እነዚህ ናቸው፤ ንስር፥ ገዲ፥ ዓሣ አውጪ፥


ነገር ግን ከእነርሱ መካከል ከእግሮቻቸው በላይ በምድር ላይ የሚዘሉባቸው ቅልጥሞች ካሉአቸው ተንቀሳቃሾች እነዚህን ትበላላችሁ፤


“በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች እነዚህ በእናንተ ዘንድ ርኩሳን ናቸው፦ ፍልፈል፥ አይጥ፥ እንሽላሊት፥


ሰኮናው ስንጥቅ የሆነውንና የሚያመሰኳውን እንስሳ ትበላላችሁ፤


የሚበላ ምግብ ሁሉ ከሸክላው ዕቃ የውሃ ነጠብጣብ ቢያርፍበት፥ ርኩስ ይሆናል፤ የሚጠጣም ነገር ቢሆን በዚያ ሸክላ ዕቃ ውስጥ ካለ ርኩስ ነው።


“ከሚበሉትም ቢሆን ማናቸውም እንስሳ ቢሞት የሚነካው ሁሉ እስከ ምሽት ርኩስ ነው።


ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኮናቸው ስንጥቅ ከሆነው የሚከተሉትን አትበሉም፤ ግመል ያመሰኳል፤ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።


“በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ካሉት ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ሁሉ ብሉ፤


ሰውን የሚያረክሰው ከአፍ የሚወጣው ነው እንጂ ወደ አፍ የሚገባው አይደለም!”


ባልተለመደ በልዩ ልዩ ዐይነት ትምህርት አትማረኩ፤ ልባችን የመብል ሥነ ሥርዓቶችን በመጠበቅ ሳይሆን በጸጋ ቢጸና መልካም ነው፤ ይህን የምግብ ሥነ ሥርዓት የተከተሉ ሰዎች ምንም አልተጠቀሙም።


እነዚህ ነገሮች የመታደስ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ በሥራ ላይ የዋሉ አፍአዊ ሥርዓቶች ናቸው፤ እነርሱ ስለ መብልና ስለ መጠጥ፥ ስለ ልዩ ልዩ የመንጻት ሥርዓቶችም ብቻ የተደረጉ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告