Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 10:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሙሴም ዑዚኤል የተባለው የአሮን አጐት ልጆች የሆኑትን ሚሻኤልንና ኤልጻፋንን ጠርቶ “ኑ የእነዚህን የወንድሞቻችሁን ሬሳ ከተቀደሰው ድንኳን አንሥታችሁ ከሰፈር ወደ ውጪ አውጡ” አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሙሴ የአሮንን አጎት የዑዝኤልን ልጆች ሚሳኤልንና ኤልዳፋንን ጠርቶ፣ “ወደዚህ ኑና ወንድሞቻችሁን አንሡ፤ ከመቅደሱም ደጃፍ አርቃችሁ፣ ከሰፈር ወደ ውጭ ውሰዷቸው” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሙሴም የአሮንን አጎት የዑዝኤልን ልጆች ሚሳኤልንና ኤልጻፋንን ጠርቶ፦ “ቅረቡ፥ ወንድሞቻችሁንም ከመቅደሱ ፊት አንሥታችሁ ከሰፈሩ ውጭ ውሰዱአቸው” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሙሴም የአ​ሮ​ንን አጎት የአ​ዚ​ሔ​ልን ልጆች ሚሳ​ዴ​ንና ኤል​ሳ​ፍ​ንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ሁን ከመ​ቅ​ደሱ ፊት አን​ሥ​ታ​ችሁ ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ውሰ​ዱ​አ​ቸው” አላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሙሴም የአሮንን አጎት የዑዝኤልን ልጆች ሚሳኤልንና ኤልጻፋንን ጠርቶ፦ ቅረቡ፥ ወንድሞቻችሁንም ከመቅደሱ ፊት አንሥታችሁ ከሰፈር ወደ ውጭ ውሰዱአቸው አላቸው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 10:4
10 交叉引用  

ቀዓትም ዓምራም፥ ይጽሐር፥ ኬብሮንና ዑዚኤል ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆችን ወለደ።


የእስራኤል ሕዝብ በሰፈሩበት ቦታ ሁሉ ሙሴ ድንኳኑን ከሰፈሩ ራቅ ባለ ቦታ ይተክለው ነበር፤ እርሱም “ድንኳን” ተብሎ ተጠራ፤ እግዚአብሔርን መጠየቅ የሚፈልግ ሁሉ ወደዚያ ይሄድ ነበር።


ቀዓት፥ ዓምራም፥ ይጽሐር፥ ኬብሮንና ዑዚኤል የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ቀዓት በሕይወት የኖረበት ዘመን 133 ዓመት ነው።


ዑዚኤልም ሚሻኤል፥ ኤልጻፋንና ሲትሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት።


የቀዓትም ወንዶች ልጆች ዓምራም፥ ይጽሐር፥ ኬብሮንና ዑዚኤል ይባሉ ነበር።


የቀዓትም ጐሣ መሪ የዑዚኤል ልጅ የሆነው ኤሊጻፋን ነበር።


ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ በር አጠገብ ሲደርስ እነሆ፥ ሰዎች ሬሳ ተሸክመው ከከተማይቱ ይወጡ ነበር፤ የሞተው ሰው ለእናቱ አንድ ነበር፤ እናቱም ባልዋ የሞተባት መበለት ነበረች፤ ከከተማይቱም ብዙ ሰዎች ተከትለዋት ነበር።


ጐልማሶች ተነሥተው አስከሬኑን ከፈኑና ወስደው ቀበሩት።


አንዳንድ መንፈሳውያን ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ አለቀሱለት።


跟着我们:

广告


广告