Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሰቈቃወ 5:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የጽዮን ተራራ ባድማ ስለ ሆነች፥ ቀበሮዎች ይመላለሱበታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ባዶዋን የቀረችው የጽዮን ተራራ፣ የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ስለ ጽዮን ተራራ፥ ባድማ ሆናለችና፥ ቀበሮችም ተመላልሰውባታልና።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የጽ​ዮን ተራራ ባድማ ሆና​ለ​ችና፥ ቀበ​ሮ​ዎ​ችም ተመ​ላ​ል​ሰ​ው​ባ​ታ​ልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ስለ ጽዮን ተራራ፥ ባድማ ሆናለችና፥ ቀበሮችም ተመላልሰውባታልና።

参见章节 复制




ሰቈቃወ 5:18
18 交叉引用  

እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤


በአጠገቡም ቆሞ የነበረው ጦቢያ በበኩሉ፦ “እነርሱ ምን ዐይነት ቅጽር መሥራት ይችላሉ? የእነርሱ ግንብ ቀበሮ እንኳ ብትወጣበት ሊፈርስ ይችላል!” ሲል በማፌዝ ተናገረ።


በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሬሳቸውንም ቀበሮዎች ይበሉታል።


አምላክ ሆይ! አምርረህ አትቈጣ፤ ኃጢአታችንንም ለዘለዓለም አታስብብን፤ እኛ ሁላችን ሕዝብህ መሆናችንን አስታውስ።


በመላ አገራችሁ በፈጸማችሁት ከፍተኛ ኃጢአት ምክንያት ያላችሁን ሀብትና ንብረት እንዲሁም መሠዊያዎቻችሁን ሁሉ በምርኮ ጠላቶቻችሁ እንዲወስዱ አደርጋለሁ።


“ ‘ይህ ቤተ መቅደስ እንደ ሴሎ ይሆናል፥’ ብለህ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገርከው ለምንድን ነው? ደግሞስ ‘ይህች ከተማ ትጠፋለች፥ በውስጥዋም ነዋሪ አይገኝባትም’ ያልከውስ ስለምንድን ነው?” ብለው ጠየቁ። ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ በቤተ መቅደስ ተሰብስበው ዙሪያዬን ከበቡኝ።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በኢየሩሳሌምና በሌሎችም የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ያመጣሁትን ጥፋት እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል፤ አሁንም እንኳ እንደ ፈራረሱ ናቸው፤ ማንም አይኖርባቸውም፤


ስለዚህም በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ቊጣዬንና መዓቴን በማፍሰስ በእሳት እንዲጋዩ አደረግሁ፤ እነርሱም ዛሬ እንደሚታዩት ሁሉ ፍርስራሾችና ባድማ ሆነዋል።


ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱንና በኢየሩሳሌም የነበሩ የታላላቅ ሰዎችን መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ታላላቅ ሕንጻዎችን አቃጠለ፤


እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሁሉም ወና ስለ ሆኑና በእነርሱም ላይ የሚዘዋወርባቸው ስለሌለ፥ ስለ ተራራዎች አዝናለሁ፤ ስለ ሜዳዎችም አለቅሳለሁ፤ የከብቶች ድምፅ ዳግመኛ አይሰማም፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ሁሉ ሸሽተው ጠፍተዋል።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አደርጋታለሁ፤ የቀበሮዎችም መፈንጫ ትሆናለች፤ የይሁዳንም ከተሞች ማንም የማይኖርባቸው ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”


የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ነቢዮቻችሁ በፍርስራሽ ቦታዎች መካከል እንደሚኖሩ ቀበሮዎች ናቸው።


አምላክ ሆይ! ጸሎቴንና ልመናዬን ስማ፤ ስለ ስምህ ስትል ለፈረሰው ቤተ መቅደስህ ራራ።


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ ቤተ መቅደሱም የተሠራበት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告