Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሰቈቃወ 4:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ቀበሮዎች እንኳን የወለዱአቸውን ከጡታቸው ይመግባሉ፤ ሕዝቤ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጎኖች ጨካኞች ሆነዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ቀበሮዎች እንኳን ግልገሎቻቸውን ለማጥባት፣ ጡታቸውን ይሰጣሉ፤ ሕዝቤ ግን በምድረ በዳ እንዳሉ ሰጎኖች፣ ጨካኞች ሆኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጋሜል። ቀበሮች እንኳ ጡቶታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፥ የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኝ ሆነች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ጋሜል። አራ​ዊት እንኳ ጡታ​ቸ​ውን ገል​ጠው ግል​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን አጠቡ፤ የወ​ገኔ ሴት ልጆች ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካ​ኞች ሆኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ጋሜል። ቀበሮች እንኳ ጡቶታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፥ የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኝ ሆነች።

参见章节 复制




ሰቈቃወ 4:3
14 交叉引用  

በማግስቱ ማለዳ ተነሥቼ ልጄን ለማጥባት ስዘጋጅ የሞተ ሆኖ አገኘሁት፤ ትኲር ብዬ ስመለከተው እኔ የወለድኩት ልጅ አለመሆኑን ተገነዘብኩ።”


በታላላቅ ሕንጻዎችዋና በቤተ መንግሥትዋ ውስጥ የጅቦችና የተኲላዎች ጩኸት ያስተጋባል፤ እነሆ በዚህ ዐይነት ባቢሎን የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል።”


ቤተ መንግሥቶችዋና በቅጽር የተመሸጉ ከተሞችዋ ሁሉ እሾኽና ሳማ ይበቅልባቸዋል፤ የቀበሮና የሰጐን መኖሪያዎች ይሆናሉ።


እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፦ “እናት የምታጠባውን ልጅዋን ልትረሳ ትችላለችን? ወይስ ለወለደችው ልጅ አትራራምን? እርስዋ እንኳ ብትረሳ እኔ ግን እናንተን አልረሳም።


ጠላት ከተማይቱን ከቦ ሕዝቡን ለመጨረስ ያስጨንቋቸዋል፤ በዚህ ጊዜ ምግብ ሁሉ አልቆ ሕዝቡ ስለሚራብ እርስ በርሳቸው ይባላሉ፤ እንዲያውም ወላጆች የልጆቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።’ ”


ጌታ ሆይ! ተመልከት! ከአሁን ቀደም እንደዚህ የጨከንክበት ሕዝብ አለ ወይ? ሴቶች የወለዱአቸውንና ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይብሉን! በጌታ ቤተ መቅደስ ውስጥስ ካህናትና ነቢያት ይገደሉን!


የርኅሩኅ ሴቶች እጆች የገዛ ልጆቻቸውን ቀቀሉ፤ ከተማዋ በተደመሰሰች ጊዜ እነዚያ የተቀቀሉ ልጆች ለሰዎች ምግብ ሆኑ።


በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም ያሉ ወላጆች በእርግጥ ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም ወላጆቻቸውን ይበላሉ፤ በዚህ ዐይነት ሁላችሁንም እቀጣለሁ፤ የተረፉትንም በአራቱ ማእዘን እበትናቸዋለሁ።


ስለዚህም ከመራባችሁ ጽናት የተነሣ የገዛ ልጆቻችሁን ለመብላት ትገደዳላችሁ።


የማያስተውሉ፥ ውል የሚያፈርሱ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ጨካኞች ናቸው።


跟着我们:

广告


广告