Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሰቈቃወ 1:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ማንም ሰው በዓላቱን ለማክበር ስለማይመጣ የጽዮን መንገዶች ጭር ይላሉ፤ በሮችዋ ሁሉ ባዶ ናቸው፤ ካህናትዋ ይቃትታሉ ልጃገረዶችዋ በሐዘን ይጨነቃሉ የጽዮንም ዕድል ፈንታ የመረረ ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ፤ በዓላቷን ለማክበር የሚመጣ የለምና፤ በበሮቿ ሁሉ የሚገባና የሚወጣ የለም፤ ካህናቷ ይቃትታሉ፤ ደናግሏ ክፉኛ ዐዝነዋል፤ እርሷም በምሬት ትሠቃያለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፥ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፥ ድንግሎችዋም ተጨነቁ እርሷም በምሬት አለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚ​መጣ የለ​ምና የጽ​ዮን መን​ገ​ዶች አለ​ቀሱ፤ በሮ​ችዋ ሁሉ ፈር​ሰ​ዋል፤ ካህ​ና​ቷም ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ደና​ግ​ሎ​ች​ዋም ተማ​ረኩ፤ እር​ስ​ዋም በም​ሬት አለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፥ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፥ ደናግሎችዋም ተጨነቁ እርስዋም በምሬት አለች።

参见章节 复制




ሰቈቃወ 1:4
19 交叉引用  

የኢየሩሳሌም በሮች እርቃንዋን ሆና በልቅሶና በሐዘን እንደ ተቀመጠች ሴት ይሆናሉ።


አድምጡ አዲስ ዜና መጥቶአል! የሰሜን መንግሥት የይሁዳን ከተሞች ወደ ምድረበዳነት ለውጦ የቀበሮዎች መመሰጊያ ለማድረግ በመራወጥ ላይ ይገኛል።”


“ይሁዳ በሐዘን ላይ ነች፤ ከተሞችዋም በሞት ጣዕር ላይ ናቸው፤ ሕዝብዋም በሐዘን ምክንያት በመሬት ላይ ተቀምጠው ያለቅሳሉ፤ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ትጮኻለች።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አደርጋታለሁ፤ የቀበሮዎችም መፈንጫ ትሆናለች፤ የይሁዳንም ከተሞች ማንም የማይኖርባቸው ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”


“ጠላቶቼ ሁሉ ማንም የሚያጽናናኝ ሰው በሌለበት እንዴት እንደምቃትትና እንደምቸገር ሰሙ፤ አንተ ያደረግኸው መሆኑንም ዐውቀው ተደሰቱ፤ በእነርሱ ላይ ልታመጣባቸው የወሰንከውን ቀን አምጣና እንደ እኔ ይሁኑ።


ወጣት ወንዶች ወፍጮ እንዲፈጩ ተገደዱ፤ ወንዶች ልጆች እንጨት በመሸከም ተንገዳገዱ።


ሽማግሌዎች ከከተማው ሸንጎ ራቁ፤ ወጣቶች ዘፈናቸውን አቆሙ።


“በዓል” ለሚባለው ጣዖት ለማጠንና ጌጣጌጥዋን አድርጋ ፍቅረኛዎችዋን በመከተል እኔን በመተዋ እቀጣታለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።


በመካከላችሁ አደገኞች አራዊትን እልካለሁ፤ እነርሱም ልጆቻችሁን ይገድላሉ፤ ከብቶቻችሁንም ያወድማሉ፤ ከእናንተ ጥቂት ሰዎች ብቻ ስለሚቀሩ ጐዳናዎቻችሁ ሁሉ ሰው አልባ ይሆናሉ።


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ ቤተ መቅደሱም የተሠራበት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告