Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 9:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ውጊያውም ቀኑን ሙሉ ቀጥሎ ዋለ፤ አቤሜሌክ ከተማይቱን ይዞ ሕዝብዋን ሁሉ ገደለ፤ ከተማይቱን አፈራረሰ፤ በምድሪቱም ላይ ጨው ዘራባት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 በዚያ ዕለት አቢሜሌክ ቀኑን ሙሉ ከተማዪቱን ሲወጋ ውሎ በመጨረሻ ያዛት፤ ሕዝቧን ፈጀ፤ ከተማዪቱንም አጠፋ፤ በላይዋም ጨው ዘራባት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 በዚያን ዕለት አቤሜሌክ ቀኑን ሙሉ ከተማይቱን ሲወጋ ውሎ በመጨረሻ ያዛት፤ ሕዝቧን ፈጀ፤ ከተማይቱንም አጠፋ፤ በላይዋም ጨው ዘራባት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 አቤ​ሜ​ሌ​ክም በዚያ ቀን ሁሉ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ጋር ተዋጋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ይዞ በእ​ር​ስዋ የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ገደለ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም አፈ​ረሰ፤ ጨውም ዘራ​ባት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 አቤሜሌክም በዚያ ቀን ሁሉ ከከተማይቱ ጋር ተዋጋ፥ ከተማይቱንም ይዞ በእርሷ የነበሩትን ሕዝብ ገደለ፥ ከተማይቱንም አፈረሰ፥ ጨውም ዘራባት።

参见章节 复制




መሳፍንት 9:45
8 交叉引用  

የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኘውን የሴኬምን ከተማ ምሽግ አድርጎ በዚያ ለጥቂት ጊዜ ቈየ፤ ከዚያም በመነሣት የፐኑኤልን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራ፤


ከተሞቻቸውን ደመሰሱ፤ ለም በሆነው እርሻ ውስጥ በሚያልፉበትም ጊዜ እያንዳንዱ እስራኤላዊ አንዳንድ ድንጋይ ይወረውርበት ስለ ነበር በመጨረሻ እርሻዎቹ ሁሉ በድንጋይ ተሸፈኑ፤ ምንጮቻቸውን ደፈኑ፤ የፍራፍሬ ዛፎቻቸውንም ሁሉ ቈረጡ፤ በመጨረሻም የአገሪቱ ዋና ከተማ የነበረችው ቂርሔሬስ ብቻ ቀረች፤ እርስዋንም ድንጋይ የሚያወነጭፉ ጦረኞች ከበው አደጋ ጣሉባት።


እዚያ ከሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን አገር እንደ ጨው ምድር የማታፈራ አደረጋት።


ነገር ግን ረግረጉና እቋሪው ውሃ የጨው መከማቻ እንደ ሆነ ይቀራል እንጂ የጠራ ውሃ አይሆንም።


እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ፥ ሞአብ እንደ ሰዶም አሞንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም በዳዋና በጨው ጒድጓድ ተወራ ለዘለቄታ ባድማ ትሆናለች፤ ከሞት የተረፈው ሕዝቤ ይበዘብዛቸዋል ንብረታቸውንም ይወርሳል።”


ምድሪቱም ሁሉ በዲንና በጨው ትሸፈናለች፤ ምንም ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አታበቅልም፤ እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው እንደ ደመሰሳቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ጺባዮ ትሆናለች።


የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።


አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር የተመደበው ቡድን የከተማይቱን ቅጽር በር ለመጠበቅ ተጣድፈው ወጥተው በከተማው መግቢያ በር ላይ ቆሙ፤ የቀሩት ሁለቱ ቡድኖች በመስኩ በተገኙት ላይ አደጋ ጥለው ፈጁአቸው።


跟着我们:

广告


广告