Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 9:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 የዓቤድ ልጅ ጋዓልም እንዲህ አለ፦ “አቤሜሌክ ማን ነው? እኛ የሴኬም ሰዎች ለእርሱ የምንገዛው ለምንድነው? የጌዴዎን ልጅና የእርሱ የጦር መሪ ዜቡር የሐሞርን አባት ሴኬምን ያገለገሉ አይደሉምን? ለምን ለእርሱ እንታዘዛለን? ይልቅስ የጐሣችሁ መሥራች ለሆነው ለሴኬም አባት ለሐሞር ታማኞች ሁኑ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የአቤድ ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፤ “እንገዛለት ዘንድ አቢሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድን ናት? እርሱ የይሩባኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የርሱ ረዳት ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፤ ለምን ለአቢሜሌክ እንገዛለን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የአቤድ ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፤ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድን ናት? እርሱ የይሩበኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ረዳት ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፤ ለምን ለአቤሜሌክ እንገዛለን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የአ​ቤ​ድም ልጅ ገዓል፥ “አቤ​ሜ​ሌክ ማን ነው? እን​ገ​ዛ​ለ​ትስ ዘንድ የሴ​ኬም ልጅ ማን ነው? እርሱ የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን? ዜቡ​ልስ የእ​ርሱ ጠባቂ አይ​ደ​ለ​ምን? ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ሰዎች ጋርስ አገ​ል​ጋዩ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ም​ንስ ለዚህ እን​ገ​ዛ​ለን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የአቤድም ልጅ ገዓል፦ የምንገዛለት አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድር ነው? እርሱ የይሩብኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልም የእርሱ ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፥

参见章节 复制




መሳፍንት 9:28
8 交叉引用  

ድንኳኑን የተከለበትን የሴኬም አባት ከነበረው ከሐሞር ዘሮች ላይ በመቶ ብር ገዛው፤


የአገሩ ገዢ የሒዋዊው የሐሞር ልጅ ሴኬም ባያት ጊዜ ያዛት፤ በማስገደድም ክብረ ንጽሕናዋን ደፈረ።


ከዚህ በኋላ የሴኬም አባት ሐሞር፥ ያዕቆብን ለማነጋገር ወጣ፤


በዚያን ጊዜ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ ጠባዩ የተበላሸ የማይረባ አንድ ሰው በጌልገላ ይኖር ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከብንያም ነገድ ሲሆን አባቱ ቢክሪ ይባላል፤ ይህም ሼባዕ እምቢልታ ነፍቶ “ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም! ከእሴይ ልጅ ጋር ምንም ዕድል ፈንታ የለንም! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እያንዳንድህ ወደ ቤትህ ግባ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ።


ሕዝቡ፥ ንጉሥ ሮብዓም ጥያቄውን እንዳልተቀበለው በተገነዘበ ጊዜ “ከዳዊት ጋር ምን ድርሻ አለን? ከእሴይ ልጅ ከዳዊት ጋር ምን ድርሻ አለን፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደየቤትህ ሂድ! ዳዊት ሆይ የራስህን ቤት ጠብቅ!” ብለው መለሱለት። ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ወደየቤቱ ሄደ።


ከዚህ በኋላ የዔቤድ ልጅ ጋዓል ከወንድሞቹ ጋር ወደ ሴኬም መጣ፤ የሴኬምም ሰዎች እምነታቸውን በእርሱ ላይ ጣሉ።


አቤሜሌክም መኖሪያውን በአሩማ አደረገ፤ ዘቡል ግን ጋዓልንና ወንድሞቹን ከሴኬም እያባረረ አስወጣቸው፤ ከዚያም በኋላ እዚያ ለመኖር አልቻሉም።


ናባልም በመጨረሻ “ኧረ ለመሆኑ ዳዊት ማን ነው? እኔ ስለ እርሱ ሰምቼም አላውቅም! እነሆ፥ በአሁኑ ጊዜ አገሪቱ ከጌቶቻቸው በኰበለሉ አገልጋዮች ተሞልታለች!


跟着我们:

广告


广告