Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 9:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ርኩስ መንፈስን ላከ፤ ስለዚህም የሴኬም ሰዎች በእርሱ ላይ ዐመፁበት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እግዚአብሔር በአቢሜሌክና በሴኬም ገዦች መካከል ክፉ መንፈስ ሰደደ፤ ስለዚህም የሴኬም ሰዎች አቢሜሌክን ከዱት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ነዋሪዎች መካከል ክፉ መንፈስ ሰደደ፤ ስለዚህም የሴኬም ሰዎች አቤሜሌክን ከዱት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክና በሰ​ቂማ ሰዎች መካ​ከል ክፉን መን​ፈስ ሰደደ፤ የሰ​ቂ​ማም ሰዎች የአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክን ቤት ከዱት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ፥ የሴኬምም ሰዎች በአቤሜሌክ ላይ ተንኰል አደረጉ።

参见章节 复制




መሳፍንት 9:23
15 交叉引用  

ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት እግዚአብሔር ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው።


ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት ይኸው ነው።


የተዘበራረቀ ምክር እንዲሰጡ ያደረጋቸውም እግዚአብሔር ነው፤ በመጨረሻም ግብጽ በሁሉ ነገር በመሳሳት የገዛ ትፋቱ አዳልጦት እንደሚጥለው ሰካራም ትንገዳገዳለች።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በግብጽ ምድር የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ አደርጋለሁ፤ ወንድም በወንድሙ ላይ፥ ጐረቤትም በጐረቤቱ ላይ በጠላትነት እንዲነሣ አደርጋለሁ፤ ከተሞች በከተሞች ላይ፥ ነገሥታት በነገሥታት ላይ በጠላትነት ተነሥተው ይዋጋሉ።


አንተ ማንም ጥፋት ሳያደርስብህ ጥፋተኛ የሆንክ! ማንም ሳይከዳህ ከዳተኛ የሆንክ ወዮልህ! ጥፋትን ማድረስህን ስታቆም ትጠፋለህ፤ ከዳተኛነትህንም ስታቆም ክዳት ይደርስብሃል።


በሌሎች ላይ በምትፈርዱበት ፍርድ፥ በእናንተም ላይ ይፈረድባችኋል፤ እንዲሁም በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።


አንድ መንግሥት ተከፋፍሎ እርስ በርሱ የሚጋጭ ከሆነ ያ መንግሥት ጸንቶ መቆም አይችልም።


ይህ ካልሆነ ግን ከአቤሜሌክ እሳት ወጥቶ የሴኬምንና የቤትሚሎንን ሰዎች ይብላ፤ እንዲሁም ከሴኬምና ከቤትሚሎ እሳት ወጥቶ አቤሜሌክን ይብላ።”


አቤሜሌክም በእስራኤል ላይ ሦስት ዓመት ነገሠ፤


跟着我们:

广告


广告