Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 9:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ይህ ካልሆነ ግን ከአቤሜሌክ እሳት ወጥቶ የሴኬምንና የቤትሚሎንን ሰዎች ይብላ፤ እንዲሁም ከሴኬምና ከቤትሚሎ እሳት ወጥቶ አቤሜሌክን ይብላ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቢሜሌክ ትውጣና እናንተን፣ የሴኬምንና የቤት ሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፣ ከሴኬምና ከቤት ሚሎን ገዦች ትውጣና አቢሜሌክን ትብላ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቤሜሌክ ትውጣና እናንተን፥ የሴኬምንና የቤትሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፥ ከሴኬምና ከቤትሚሎን ነዋሪዎች ትውጣና አቤሜሌክን ትብላ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እን​ዲህ ባይ​ሆን ግን ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰ​ቂ​ማ​ንም ሰዎች፥ የመ​ሐ​ሎ​ን​ንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይ​ሆን ከሰ​ቂማ ሰዎች ከመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ትብ​ላው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እንዲህ ባይሆን ግን ከአቤሜሌክ እሳት ይውጣ፥ የሴኬምንም ሰዎች ቤትሚሎንም ይብላ፥ ከሴኬምም ሰዎች ከቤትሚሎም እሳት ይውጣ፥ አቤሜሌክንም ይብላ።

参见章节 复制




መሳፍንት 9:20
14 交叉引用  

የእሳት ፍም በላያቸው ይውደቅ፤ ወደ ጒድጓድም ይጣሉ፤ ከዚያም ከቶ አይውጡ።


ስለ ፈጸሙት በደል ተገቢ ዋጋቸውን ክፈላቸው፤ በእጃቸው ስለ ፈጸሙት ክፉ ሥራ ፍረድባቸው፤ ተገቢ ቅጣታቸውንም ስጣቸው።


ሦስት መቶው የጌዴዎን ሰዎች እምቢልታቸውን በሚነፉበት ጊዜ እግዚአብሔር እያንዳንዱን የጠላት ወታደር በጓደኛው ላይና በሠራዊቱ ላይ ሰይፉን እንዲያነሣ አደረገ፤ ሠራዊቱም ፊታቸውን ወደ ጽሬራ በመመለስ እስከ ቤትሺጣ፥ ከዚያም አልፎ በጣባት አጠገብ እስካለው አቤልመሖላ ድረስ ሸሽተው ሄዱ።


የእሾኽ ቊጥቋጦም ‘በእርግጥ ንጉሥ ልታደርጉኝ ከፈለጋችሁ፥ ኑና በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ከእሾኻማዎቹ ቅርንጫፎቼ እሳት ወጥቶ የሊባኖስ ዛፍን ያቃጥላል’ ሲል መለሰላቸው።”


እንግዲህ ዛሬ ለጌዴዎንና ለቤተሰቡ ያደረጋችኹት በቅንነትና ተገቢ በሆነ መንገድ ከሆነ ከአቤሜሌክ ጋር ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ደስ ይበለው፤


ኢዮአታም ይህን ከተናገረ በኋላ ወንድሙን አቤሜሌክን ስለ ፈራ ሸሽቶ ወደ በኤር ሄዶ እዚያ ተቀመጠ።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ርኩስ መንፈስን ላከ፤ ስለዚህም የሴኬም ሰዎች በእርሱ ላይ ዐመፁበት።


አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር የተመደበው ቡድን የከተማይቱን ቅጽር በር ለመጠበቅ ተጣድፈው ወጥተው በከተማው መግቢያ በር ላይ ቆሙ፤ የቀሩት ሁለቱ ቡድኖች በመስኩ በተገኙት ላይ አደጋ ጥለው ፈጁአቸው።


ከዚያን በኋላ የሴኬምና የቤትሚሎ ሕዝብ በአንድነት ተሰብስበው፥ በሴኬም ወደሚገኘው ወደተቀደሰው ወርካ ዛፍ ሄዱ፤ በዚያም አቤሜሌክን አነገሡ።


跟着我们:

广告


广告