Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 8:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የሱኮት መሪዎች ግን “ለአንተ ሠራዊት ምግብ የምንሰጠው በምን ምክንያት ነው? ዜባሕንና ጻልሙናዕን ገና አልማረክህም” አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የሱኮት ሹማምት ግን፣ “ለተከተሉህ ሰዎች እንጀራ እንሰጥ ዘንድ ዛብሄልና ስልማና በእጅህ ገብተዋልን?” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የሱኮት ሹማምንት ግን፥ “ለተከተሉህ ሰዎች እንጀራ እንሰጥ ዘንድ ዜባሕና ጻልሙና በእጅህ ገብተዋልን?” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የሱ​ኮ​ትም አለ​ቆች፥ “እኛ ለሠ​ራ​ዊ​ትህ እህል እን​ድ​ን​ሰጥ የዛ​ብ​ሄ​ልና የስ​ል​ማና እጅ አሁን በእ​ጅህ ነውን?” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የሱኮትም አለቆች፦ እኛ ለሠራዊትህ እንጀራ እንድንሰጥ የዛብሄልና የስልማና እጅ አሁን በእጅህ ነውን? አሉ።

参见章节 复制




መሳፍንት 8:6
11 交叉引用  

ከዚህ በታች በዕድሜአቸው ቅደም ተከተል ተራ የተዘረዘሩትን ልጆች ወለደ፤ እነርሱም፦ ነባዮት፥ ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥


ከዚህ በኋላ ምሳ ለመብላት ተቀመጡ፤ በሚመገቡበትም ጊዜ እስማኤላውያን ነጋዴዎችን በሩቅ አዩ፤ እነርሱም በግመሎቻቸው ቅመማ ቅመም፥ በለሳን፥ ከርቤም ጭነው ከገለዓድ ወደ ግብጽ የሚጓዙ ነበሩ።


የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማኤላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጒድጓድ ጐትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይዘውት ሄዱ።


ንጉሥ አክዓብ መልእክተኞቹን “ ‘እውነተኛ ወታደር መደንፋት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም’ ብላችሁ ለንጉሥ ቤንሀዳድ ንገሩት” ሲል መለሰላቸው።


ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት “አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኲርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‘ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ’ ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኲርንችት ሞተች፤


ድኻ እየተለማመጠ በትሕትና ይናገራል፤ ሀብታም ግን በትምክሕት ይመልሳል።


ሌሎቹ ግን የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ያሳድዳሉ እንጂ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ግድ የላቸውም።


የእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለ፤ “ሜሮዝን ርገሙ! እዚያ የሚኖሩትን ሁሉ ፈጽማችሁ ርገሙ! እነርሱ በእግዚአብሔር ጐን አልቆሙም፤ ስለ እርሱም ለመዋጋት አልተሰለፉም።”


ከዚህ በኋላ ጌዴዎን ወደ ሱኮት ሰዎች መጥቶ “ ‘ዜባሕንና ጻልሙናዕን ገና አልማረክህም፤ ታዲያ አሁን በረሀብ ለደከሙት ወታደሮችህ ምግብ የምንሰጠው ለምንድን ነው?’ ብላችሁ አሹፋችሁብኝ ነበር፤ አሁን ግን ዜባሕና ጻልሙናዕ እነሆ በእጄ ይገኛሉ!” አላቸው።


ወደ ሱኮት በደረሱም ጊዜ ጌዴዎን ለከተማይቱ ሰዎች እንዲህ አለ፤ “እስቲ ለሰዎቼ እንጀራ ስጡልኝ፤ እነርሱ እጅግ ደክመዋል፤ እኔም ዜባሕና ጻልሙናዕ የተባሉትን የምድያማውያን ነገሥታት በማሳደድ ላይ ነኝ።”


跟着我们:

广告


广告