Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 7:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከእኩለሌሊት ጥቂት ቀደም ብሎ፥ ዘብ ጠባቂዎች ከተቀያየሩ በኋላ ጌዴዎንና ከእርሱ ጋር የተመደቡት መቶ ሰዎች ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ እምቢልታዎቻቸውን ነፉ፤ የያዙትንም ማሰሮ ሁሉ ሰባበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ዘቦቹ ተቀያይረው የእኩለ ሌሊቱን ጥበቃ በጀመሩበት ጊዜ፣ ጌዴዎንና ዐብረውት የነበሩት መቶ ሰዎች በሰፈሩ ዳርቻ ደረሱ፤ እነርሱም ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ የያዟቸውንም ማሰሮዎች ሰበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ዘቦቹ ተቀያይረው የእኩለ ሌሊቱን ጥበቃ በጀመሩበት ጊዜ፥ ጌዴዎንና አብረውት የነበሩት መቶ ሰዎች በሰፈሩ ዳርቻ ደረሱ፤ እነርሱም ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ የያዟቸውንም ማሰሮች ሰበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ጌዴ​ዎ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት መቶ ሰዎች በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው ትጋት መጀ​መ​ሪያ ዘብ ጠባ​ቂ​ዎች ሳይ​ነቁ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ች​ንም ነፉ፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ማሰ​ሮ​ዎች ሰባ​በሩ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጌዴዎንም ከእርሱም ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች በመካከለኛው ትጋት ትጋቱም በተጀመረ ጊዜ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፥ ቀንደ መለከቶችንም ነፉ፥ በእጃቸውም የነበሩትን ማሰሮች ሰባበሩ።

参见章节 复制




መሳፍንት 7:19
11 交叉引用  

በብረት በትር ትሰብራቸዋለህ፤ እንደ ሸክላ ዕቃም ቀጥቅጠህ ታደቃቸዋለህ’ ” አለኝ።


ለአንተ አንድ ሺህ ዓመት እንደ አንድ ቀን ነው፤ አልፎ እንደ ሄደው እንደ ትናንት ነው፤ እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓቶች ነው።


ገና ጎሕ ሳይቀድ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዐምድ ሆኖ የግብጻውያንን ሠራዊት በተመለከተ ጊዜ ሁሉም በፍርሃት ተጨነቁ።


“እኩለ ሌሊት ሲሆን ግን ‘እነሆ፥ ሙሽራው መጣ! ውጡና ተቀበሉት!’ የሚል ውካታ ተሰማ።


የጌታ ቀን የሚመጣው፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ ዐይነት መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ደኅና አድርጋችሁ ታውቃላችሁ።


“እነሆ! እኔ እንደ ሌባ በድንገት እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይሆንና ኀፍረቱን ሰዎች እንዳያዩበት ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው የተመሰገነ ነው!”


ሦስት መቶዎቹንም ሰዎች ከፍሎ በሦስት ቡድን መደባቸው፤ ለእያንዳንዱም ሰው አንድ እምቢልታና በውስጡ ችቦ ያለበት አንድ ማሰሮ ሰጠ።


እኔና ከእኔ ጋር የተመደቡት ሰዎች በቀንደ መለከቶቻችን ድምፅ ስናሰማ፥ እናንተም የራሳችሁን እምቢልታ ድምፅ በሰፈሩ ዙሪያ እያሰማችሁ ‘ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን ተዋጉ!’ ብላችሁ ጩኹ።”


በሌላም በኩል የነበሩት ሁለቱ ክፍሎች እንዲሁ አደረጉ፤ ሁሉም የተለኰሱትን ችቦዎቻቸውን በግራ እጃቸው፥ እምቢልታቸውን በቀኝ እጃቸው ይዘው “ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን እንዋጋለን!” እያሉ በመጮኽ ደነፉ።


跟着我们:

广告


广告