Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 6:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የምድያማውያን ኀይል በእስራኤል ላይ በረታ፤ በእነርሱም ምክንያት የእስራኤል ሕዝብ መሸሸጊያ ቦታ፥ ዋሻና ምሽግ አዘጋጁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እስራኤላውያን የምድያማውያን ኀይል ስለ በረታባቸው በየዋሻውና በየምሽጉ፣ በየተራራው ጥግ መሸሸጊያ ስፍራ አበጁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እስራኤላውያን የምድያማውያን ኃይል ስለበረታባቸው በየዋሻውና በየምሽጉ፥ በየተራራው ጥግ መሸሸጊያ ስፍራ አበጁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የም​ድ​ያ​ምም እጅ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠነ​ከ​ረች፤ ከም​ድ​ያ​ምም ፊት የተ​ነሣ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በተ​ራ​ሮ​ችና በገ​ደ​ሎች ላይ ጕድ​ጓ​ድና ዋሻ፥ ምሽ​ግም አበጁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የምድያምም እጅ በእስራኤል ላይ ጠነከረች፥ ከምድያምም የተነሣ የእስራኤል ልጆች በተራራ ላይ ጉድጓድና ዋሻ ምሽግም አበጁ።

参见章节 复制




መሳፍንት 6:2
12 交叉引用  

መኖሪያቸውንም በየዋሻውና በየገደሉ ሥር በተቈፈሩ ጒድጓዶች ውስጥ ለማድረግ ተገደዱ።


እነዚያን ሰዎች ገድሎ የጣለበትም ያ ጒድጓድ የእስራኤል ንጉሥ ባዕሻ አደጋ በጣለበት ጊዜ ንጉሥ አሳ ለመጠባበቂያ አስቈፍሮት የነበረ ትልቅ ጒድጓድ ነበር፤ እስማኤል ያን ጒድጓድ በሬሳ ሞላው።


“የሞአብ ነዋሪዎች ሆይ! ከተሞቻችሁን ለቃችሁ በገደል አፋፍ ጎጆዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ በመሆን በቋጥኞች መካከል ኑሩ።


ፊቴን በቊጣ እመልስባችኋለሁ፤ በጠላቶቻችሁም ትሸነፋላችሁ የሚጠሉአችሁም ይገዙአችኋል፤ ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።


በበረሓ፥ በተራራ፥ በምድር ውስጥ ባሉ ዋሻዎችና ፈፋዎች ዞሩ። በዚህም ዐይነት ዓለም ለእነርሱ ተገቢ ስፍራ ሆና አልተገኘችም።


የምድር ነገሥታት፥ ገዢዎች፥ የጦር አለቆች፥ ሀብታሞች፥ ኀይለኞች፥ አገልጋዮችና ጌቶችም ሁሉ በዋሻዎችና በተራራዎች አለቶች ውስጥ ተሸሸጉ፤


አሞናውያንና ፍልስጥኤማውያንም ከዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን ምድር በገለዓድ ውስጥ የሚኖሩትን እስራኤላውያንን ለዐሥራ ስምንት ዓመት አስጨንቀው ገዙአቸው።


ዐሞናውያን የይሁዳን፥ የብንያምንና የኤፍሬምን ነገዶች ለመውጋት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ እስራኤላውያንም እጅግ ተጨነቁ።


እስራኤላውያን ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ምድያማውያን፥ ከዐማሌቃውያንና የምሥራቅ ሰዎች እየመጡ አደጋ ይጥሉባቸው ነበር።


እስራኤላውያን ሁኔታው አስጊ መሆኑን ባዩና ሠራዊቱም መዋከቡን በተመለከቱ ጊዜ በዋሻ፥ በሾኽ ቊጥቋጦ፥ በአለቶች መካከል በጒድጓዶችና በጒድባ ውስጥ ተሸሸጉ፤


እነርሱም ወጣ ብለው ለፍልስጥኤማውያን ታዩአቸው፤ ፍልስጥኤማውያንም “እነሆ! አንዳንድ ዕብራውያን ከተሸሸጉበት ጒድጓድ በመውጣት ላይ ናቸው!” ተባባሉ፤


跟着我们:

广告


广告