Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 6:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ጌዴዎንም ወደ ቤት ገባና የፍየል ጠቦት ዐርዶ አዘጋጀ፤ ዐሥር ኪሎ የሚያኽልም ዱቄት ወስዶ እርሾ ያልገባበት እንጀራ ጋገረ፤ ሥጋውን በመሶብ፥ መረቁን በምንቸት አድርጎ በወርካው ሥር ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር መልአክ ወስዶ አቀረበለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ጌዴዎን ወደ ቤቱ ሄደ፤ የፍየል ጠቦትም ዐረደ፤ አንድ ኢፍ መስፈሪያ ዱቄት ወስዶ ቂጣ ጋገረ። ሥጋውን በቅርጫት፣ መረቁን በምንቸት ይዞ በመምጣት በባሉጥ ሥር ለተቀመጠው አቀረበለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጌዴዎን ወደ ቤቱ ሄደ፤ የፍየል ጠቦትም ዐረደ፤ አንድ ኢፍ መስፈሪያ ዱቄት ወስዶ እርሾ ያልገባበት ቂጣ ጋገረ። ሥጋውን በቅርጫት፥ መረቁን በምንቸት ይዞ በመምጣት በባሉጥ ሥር ለተቀመጠው አቀረበለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ጌዴ​ዎ​ንም ሄደ፤ የፍ​የ​ሉ​ንም ጠቦት፥ የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያም ዱቄት የቂጣ እን​ጎቻ አዘ​ጋጀ፤ ሥጋ​ው​ንም በሌ​ማት አኖረ፤ መረ​ቁ​ንም በም​ን​ቸት ውስጥ አደ​ረገ፤ ሁሉ​ንም ይዞ በዛፍ በታች አቀ​ረ​በ​ለት። ሰገ​ደ​ለ​ትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጌዴዎን ገባ የፍየሉንም ጠቦት የኢፍ መስፈሪያም ዱቄት የቂጣ እንጎቻ አዘጋጀ፥ ሥጋውን በሌማት አኖረ፥ መረቁንም በምንቸት ውስጥ አደረገ፥ ሁሉንም ይዞ በአድባሩ ዛፍ በታች አቀረበለት።

参见章节 复制




መሳፍንት 6:19
9 交叉引用  

እንዲህም አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፥ አልፈኸኝ እንዳትሄድ እለምንሃለሁ፤


ወደ እኔ ወደ አገልጋያችሁ በመምጣታችሁ ደስ ብሎኛል፤ ስለዚህ ለጒዞአችሁ ብርታት የሚሰጣችሁን ጥቂት ምግብ አምጥቼ እንዳስተናግዳችሁ ፍቀዱልኝ።” እነርሱም “መልካም ነው፤ እንዳልከው አድርግ” አሉት።


መባው በምድጃ የተጋገረ ከሆነም እርሾ ያልነካው ይሁን፤ እርሱም የወይራ ዘይት ተደባልቆበት ከላመ ዱቄት የተጋገረ ዳቦ ወይም በዘይት የታሸ ቂጣ መሆን አለበት።


ደግሞም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፦ “መንግሥተ ሰማይ አንዲት ሴት ወስዳ ከሦስት መስፈሪያ ዱቄት ጋር የለወሰችውን እርሾ ትመስላለች፤ እርሾውም ሊጡን ሁሉ እንዲቦካ አደረገው።”


ነበልባሉ ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ ማኑሄና ሚስቱ እየተመለከቱ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ሆኖ ወደ ላይ ወጣ፤ እነርሱም በግንባራቸው በመሬት ላይ ተደፉ።


ምግብ የሚሆን ቊርባን እስካመጣልህም ድረስ እባክህ ከዚህ ስፍራ አትሂድ” አለው። እግዚአብሔርም “አንተ እስክትመለስ ድረስ እቈያለሁ” አለው።


መልአኩም “ሥጋውንና እንጀራውን በዚህ አለት ላይ አስቀምጠህ መረቁን በላዩ አፍስስበት” ሲል አዘዘው፤ ጌዴዎንም እንደታዘዘው አደረገ።


跟着我们:

广告


广告