Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 5:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 የሲሣራ እናት በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ በዐይነ ርግብ ቀዳዳም አተኲራ አየች፤ “የልጄ ሠረገላ ለምን ዘገየ? የሠረገላዎቹ ፈረሶች የኮቴ ድምፅስ ለምን ዘገየ?” ስትል ጠየቀች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 “የሲሣራ እናት በመስኮት ተመለከተች፤ በዐይነ ርግቡ ቀዳዳም ጮኻ ተጣራች፤ ‘ለምን ሠረገላው ሳይመጣ ዘገየ? የሠረገሎቹስ ድምፅ ለምን ጠፋ?’ አለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከመስኮት ሆና ተመለከተች፥ የሲሣራ እናት በሰቅሰቅ ዘልቃ፦ “ስለምን ለመምጣት ሠረገላው ዘገየ? ስለ ምንስ የሠረገላው መንኰራኵር ቈየ?” ብላ ጮኸች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የሲ​ሣራ እናት በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ በሰ​ቅ​ሰ​ቅም ዘልቃ፦ ከሲ​ሣራ የተ​መ​ለሰ እን​ዳለ አየች፤ ስለ​ምን ለመ​ም​ጣት ሰረ​ገ​ላው ዘገየ? ስለ​ም​ንስ የሰ​ረ​ገ​ላው መን​ኰ​ራ​ኵር ቈየ? ብላ ጮኸች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ከመስኮት ሆና ተመለከተች፥ የሲሣራ እናት በሰቅሰቅ ዘልቃ፦ ስለ ምን ለመምጣት ሰረገላው ዘገየ? ስለ ምንስ የሰረገላው መንኰራኵር ቈየ? ብላ ጮኸች።

参见章节 复制




መሳፍንት 5:28
8 交叉引用  

በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ በብርቱ ስለ ቈሰለ ታሞ ነበር፤ እርሱም “እኔ ከዚህ ሕመም እድን ወይም አልድን እንደ ሆነ በፍልስጥኤም የዔክሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡልን ጠይቃችሁልኝ ኑ” ብሎ መልእክተኞቹን ላከ።


ከዕለታት አንድ ቀን በቤቴ መስኮት ወደ ውጪ እመለከት ነበር፤


ውዴ፥ ዋልያ ወይም የአጋዘን ግልገል ይመስላል፤ እነሆም ከቤታችን ቅጽር አጠገብ ቆሞአል፤ በመስኮትም ወደ ውስጥ ይመለከታል፤ በዐይነ ርግቡ ቀዳዳ በኩል አሾልኮ ይቃኛል።


ውዴ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤ የቅመም ተክሎች በሚበቅሉባቸው ተራራዎች ላይ የሚዘል አጋዘን ወይም የዋልያ ግልገል ምሰል።


ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ጌታ እስኪመጣ ድረስ በትዕግሥት ጠብቁ፤ ገበሬ መሬቱ የመጀመሪያውንና የኋለኛውን ዝናብ እስከሚያገኝ እየታገሠ ክቡር ዋጋ ያለውን የመሬቱን ፍሬ ይጠባበቃል።


ባራቅ ከሠራዊቱ ጋር አደጋ በጣለ ጊዜ እግዚአብሔር ሲሣራን ከሠረገሎቹና ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር በአደናጋሪ ሁከት ላይ እንዲወድቅ አደረገው፤ ሲሣራም ከሠረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ።


በእግሮችዋ ሥር ተዝለፍልፎ ወደቀ፤ በእግሮችዋ ሥር ተደፋ፤ በወደቀበትም በዚያው ሞተ።


ጥበበኞች የሆኑ ወይዛዝሮችዋም መልስ ሰጡአት፤ በእርግጥ እርስዋ ለራስዋ መልስዋን አገኘች።


跟着我们:

广告


广告