Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 5:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ቀድሞ ዐማሌቃውያን ይኖሩበት ከነበረው ከኤፍሬም ወታደሮች መጡ፤ ሌሎችም ከብንያም መጡ። ከማኪር መሪዎች፥ ከዛብሎንም በትረ መንግሥትን የሚይዙ መጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 መሠረታቸው ከአማሌቅ የሆነ አንዳንዶች ከኤፍሬም መጡ፤ ብንያም አንተን ከተከተሉ ሰዎች ጋራ ነበር፤ የጦር አዛዦች ከማኪር፣ የሥልጣን በትር የያዙም ከዛብሎን ወረዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ፥ በሕዝብህ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፥ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በአ​ማ​ሌቅ ዘንድ ሥር የነ​በ​ራ​ቸው እነ​ርሱ ከኤ​ፍ​ሬም፥ ብን​ያም ሆይ! በሕ​ዝብ መካ​ከል ከአ​ንተ በኋላ ወረዱ፤ አለ​ቆች ከማ​ኪር፥ የን​ጉ​ሥ​ንም ዘንግ የሚ​ይዙ ከዛ​ብ​ሎን ወረዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ፥ በሕዝብህ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፥ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።

参见章节 复制




መሳፍንት 5:14
14 交叉引用  

ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው።


የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮርና ዛብሎን ናቸው።


የራሔል ልጆች፥ ዮሴፍና ብንያም ናቸው።


በመጀመሪያ በቊጥር ትንሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ፤ ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎች ከነጭፍሮቻቸው ታዩ። በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ።


ለጦርነት እንዲወጡ በገባዖን የመለከት፥ በራማም የጥሩንባ ድምፅ አሰሙ! በቤትአዌን “የብንያም ነገድ ሆይ! ከአንተ ጋር ነን” እያላችሁ ጩኹ!


ከዚያም በኋላ ዓብዶን ሞተ፤ ኮረብታማም በሆነው በዐማሌቃውያን አገር በኤፍሬም ግዛት በምትገኘውም በፒርዓቶን ተቀበረ።


ዔግሎንም ዐሞናውያንንና ዐማሌቃውያንን አስተባብሮ እስራኤልን ወጋ፤ የተምር ዛፍ የሞላባትንም የኢያሪኮን ከተማ በቊጥጥራቸው ሥር አደረጉ።


እዚያም ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር እንደ ደረሰ በኤፍሬም ተራራማው አገር የክተት እምቢልታ ነፋ፤ የእስራኤልም ሕዝብ በእርሱ መሪነት ተከትለውት ወረዱ።


ባራቅም የንፍታሌምንና የዛብሎንን ነገዶች ወደ ቃዴስ አስጠራ፤ ከእነርሱም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከተሉት፤ ዲቦራም አብራው ዘመተች።


ዲቦራም ባራቅን “እግዚአብሔር አንተን በሲሣራ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ የሚያደርግበት ቀን ዛሬ ስለ ሆነ ተነሥ! እነሆ! እግዚአብሔር ይመራሃል” አለችው፤ ባራቅም ዐሥር ሺህ ወታደሮች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ።


ከዚህ በኋላ ቀሪዎቹ ወደ መኳንንቱ ወረዱ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ ስለ እኔ ኀያላኑን ለመውጋት ወረዱ።


跟着我们:

广告


广告