Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እነሆ አድምጡ! ውሃ በሚቀዳባቸው ጒድጓዶች ዙሪያ የሚሰማው የብዙ ሰዎች ድምፅ፥ የእግዚአብሔርን ድል ያበሥራል፤ የእስራኤልንም ሕዝብ ድል አድራጊነት ይናገራል። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ፥ ከከተሞቻቸው ተሰልፈው ወረዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የዝማሬ ድምፅ ስሙ። ይህም የእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራ፣ ጦረኞቹም በእስራኤል ያደረጉትን ያስታውሳል። “ከዚያም የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣ ወደ ከተማዪቱ በሮች ወረዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በማጠጫው መካከል ካሉት ከቀስተኞች ጩኸት ርቀው፥ በዚያ የጌታን ጽድቅ፥ በእስራኤል ላይ የግዛቱን ጽድቅ ይጫወታሉ፥ ከዚያም በኋላ የጌታ ሕዝብ ወደ በሮች ወረዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በብ​ዙ​ዎች ደስ​ተ​ኞች መካ​ከል መሰ​ን​ቆን ምቱ፤ በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ድቅ ሥራን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ውስጥ ጽድ​ቅ​ንና ኀይ​ልን ያቀ​ር​ባሉ። ያን​ጊ​ዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ወደ ከተ​ማ​ዎቹ ወረዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በማጠጫው መካከል ካሉት ከቀስተኞች ጩኸት ርቀው፥ በዚያ የእግዚአብሔርን ጽድቅ፥ በእስራኤል ላይ የግዛቱን ጽድቅ ይጫወታሉ፥ ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ በሮች ወረዱ።

参见章节 复制




መሳፍንት 5:11
19 交叉引用  

እዚያ በደረሰ ጊዜ ከከተማው ውጪ ባለ የውሃ ጒድጓድ አጠገብ ግመሎቹ ተንበርክከው እንዲያርፉ አደረገ፤ ሰዓቱም ሊመሽ ተቃርቦ፥ ሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚወጡበት ጊዜ ነበር፤


እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውሃ ጒድጓድ አየ፤ በሦስት የተከፈሉ የበግ መንጋዎች በጒድጓዱ ዙሪያ ነበሩ፤ መንጋዎቹ ውሃ የሚጠጡት ከዚሁ ጒድጓድ ነበር፤ ጒድጓዱም የሚዘጋበት ድንጋይ ትልቅ ነበር፤


መንጋዎቹ ሁሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ ድንጋዩን አንከባለው ከጒድጓዱ ውሃ ያጠጡአቸው ነበር፤ መንጋዎቻቸውን ካጠጡ በኋላ ግን ድንጋዩን መልሰው በጒድጓዱ አፍ ላይ ይከድኑታል።


ወደ ከተማም አደባባይ እየሄድኩ በሸንጎ እቀመጥ በነበረ ጊዜ፥


ስለ ደግነትህ ገናናነት ይናገራሉ፤ ስለ ጽድቅህ ኀይል ከፍ ባለ ድምፅ ይዘምራሉ።


ምንም እንኳ ማስተዋል ቢያዳግተኝ፥ አንደበቴ ስለ ትክክለኛ ፍርድህና ስለ አዳኝነትህ ቀኑን ሙሉ ይናገራል።


ከደኅንነት ምንጭ ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።”


በዳኝነት ለሚያገለግሉት የፍትሕ ጥበብ ይሰጣቸዋል፤ የከተማይቱን የቅጽር በሮች ከጠላት ለሚከላከሉትም ኀይልን ይሰጣቸዋል።


ለምንጠጣው ውሃ ዋጋ እንከፍልበታለን፤ የማገዶ እንጨት እንኳ በዋጋ መግዛት አለብን።


በበረሓው ግድያ ስላለ ምግባችንን ማግኘት የምንችለው ሕይወታችንን ለአደጋ በማጋለጥ ነው።


ሕዝቤ ሆይ! የሞአብ ንጉሥ ባላቅ ምን እንደ ዐቀደብህና የቢዖር ልጅ በለዓም ምን እንደ መለሰለት አስታውስ፤ ከሺጢም ተነሥተህ ወደ ጌልጌላ በምትሄድበት ጊዜ በመንገድ ላይ የሆነውን ሁሉ አስታውስ፤ ይህን ሁሉ ብታስታውስ አንተን ለማዳን ያደረግኹትን ሁሉ ታውቃለህ።”


ሁለቱንም ከከተማይቱ ወደ ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉ፤ ልጃገረዲቱ መሞት የሚገባት ሰው ሊሰማ በሚችልበት ከተማ ውስጥ እያለች ርዳታ እንዲደረግላት የጩኸት ድምፅ ባለማሰማትዋ ነው፤ ሰውየውም የሚሞትበት ምክንያት ለሌላ ሰው ከታጨች ልጃገረድ ጋር በመተኛት ሕግን በማፍረሱ ነው፤ በዚህ ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።


የመሪነት ድርሻ ስለ ተቀመጠለት፥ ለራሱ የተሻለውን መሬት መረጠ፤ የሕዝብ አለቆች በተሰበሰቡ ጊዜ የእግዚአብሔርን ፈቃድና ሥርዓቱን ለእስራኤል ፈጸመ።”


የእስራኤላውያን ወጣት ሴቶች ልጆች በየዓመቱ ለአራት ቀን ያኽል ከቤታቸው ርቀው እየሄዱ ለገለዓዳዊው ለዮፍታሔ ሴት ልጅ ማዘናቸውና ማልቀሳቸው የተለመደ ሆነ።


እስራኤላውያን ቀድሞ የማያውቁአቸውን ባዕዳን አማልክትን በመረጡ ጊዜ፥ በምድሪቱ ላይ ጦርነት ሆነ፤ ከአርባ ሺህ እስራኤላውያን ጋሻና ጦር የያዘ አንድ ሰው እንኳ አልነበረም!


እንግዲህ ተነሥታችሁ ባላችሁበት ቁሙ፤ የቀድሞ አባቶቻችሁንና እናንተን ለማዳን እግዚአብሔር ያደረገላችሁን ድንቅ ሥራዎች ሁሉ በማስታወስ እነሆ እኔ በእግዚአብሔር ፊት እፋረዳችኋለሁ፤


跟着我们:

广告


广告