Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 4:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኤሁድ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ናዖድ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ኤሁድ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ ናዖድ ግን ሞቶ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ናዖድም ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ።

参见章节 复制




መሳፍንት 4:1
12 交叉引用  

እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።


እንግዲህ ሌላ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎን፥ ስለ ባራቅ፥ ስለ ሶምሶን፥ ስለ ዮፍታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙኤል፥ ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥረኛል፤


እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፤ በፍትሕ አስተዳደሩ፤ የተሰጣቸውንም ተስፋ አገኙ፤ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፤


እስራኤላውያን ባዓልና ዐስታሮት የተባሉትን ባዕዳን አማልክት እንዲሁም የሶርያን፥ የሲዶናን፥ የሞአብን፥ የዐሞንንና የፍልስጥኤምን አማልክት በማምለክ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ እርሱንም ማምለክ ተዉ፤


ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ክፉ ሥራ በመሥራት እግዚአብሔርን በደሉ። በዓሊም ተብለው የሚጠሩትን ባዕዳን አማልክት አመለኩ፤


የእስራኤል ሕዝብ እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረጉ፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር የሞአቡን ንጉሥ ዔግሎንን ከእስራኤል ይበልጥ የበረታ እንዲሆን አደረገው።


የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረጉ፤ አምላካቸውን እግዚአብሔርንም ትተው በዓልና አሼራን አመለኩ፤


የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እንደገና በደሉ፤ እግዚአብሔርም ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰባት ዓመት ሙሉ ገዙአቸው፤


跟着我们:

广告


广告