Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 3:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ኤሁድ ኀምሳ ሳንቲ ሜትር የሚያኽል ርዝመት ያለው በሁለት በኩል ስለ ታም የሆነ ሰይፍ ለራሱ አሠራ፤ እርሱንም በቀኝ ጭኑ በኩል በልብሱ ውስጥ ታጠቀው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እርሱም በሁለት በኩል ስለታም የሆነና አንድ ክንድ ተኩል ርዝመት ያለው ሰይፍ አዘጋጅቶ በልብሱ ውስጥ በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እርሱም በሁለት በኩል ስለታም የሆነና አንድ ክንድ ተኩል ርዝመትተ ያለው ሰይፍ አዘጋጅቶ በልብሱ ውስጥ በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ናዖ​ድም ሁለት አፍ ያላት ርዝ​መቷ አንድ ስን​ዝር የሆ​ነች ሰይፍ አበጀ፤ ከል​ብ​ሱም በታች በቀኝ በኩል በወ​ገቡ ታጠ​ቃት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ናዖድም ሁለት አፍ ያለው ርዝመቱ አንድ ክንድ የሆነ ሰይፍ አበጀ፥ ከልብሱም በታች በቀኝ ጭኑ በኩል አደረገው።

参见章节 复制




መሳፍንት 3:16
10 交叉引用  

በገባዖን ወደሚገኘው ወደ ትልቁ ድንጋይ በደረሱ ጊዜ ዐማሣ አገኛቸው፤ በዚህን ጊዜ ኢዮአብ ሰይፉን በሰገባው ከቶ፥ ሰገባውንም በመታጠቂያው ላይ አስሮ ለጦርነት ተዘጋጅቶ ነበር፤ እየተራመደ ወደ ፊት ሲሄድ ሳለም ሰይፉ ወደቀ፤


ስለ ታም ሰይፍ በእጆቻቸው ይዘው እልል እያሉ እግዚአብሔርን በከፍተኛ ድምፅ ያመስግኑት።


በክብርና በግርማ የተሞላህ ኀያል ንጉሥ ሆይ፥ ሰይፍህን ታጠቅ።


ሁሉም በሰይፍ አያያዝ የሠለጠኑና በጦርነትም የተፈተኑ ናቸው፤ በሌሊት ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመመከት እያንዳንዱ ሰይፉን እንደ ታጠቀ ያድራል።


የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነው፤ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ ስለታም ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፥ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ የሚቈራርጥ ነው፤ በልብ ውስጥ የተሰወረውንም ሐሳብና ምኞት መርምሮ የሚፈርድ ነው።


በቀኝ እጁ ሰባት ኮከቦችን ይዞ ነበር፤ በሁለት በኩል ስለት ያለው ሰይፍ ከአፉ ይወጣ ነበር፤ ፊቱም በሙሉ ድምቀቱ እንደሚያበራ ፀሐይ ነበረ።


“ለጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ በሁለት በኩል ስለት ያለውን ሰይፍ ከያዘው የተነገረ ነው፤


ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ነገድ ግራኝ የነበረውን የጌራን ልጅ ኤሁድን አዳኝ አድርጎ አስነሣቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞአብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት።


ከዚያን በኋላ ሰውነቱ በጣም ወፍራም ለነበረው ለዔግሎን ግብሩን ይዞ ሄደ።


ኤሁድም ሰይፉን ከቀኝ ጭኑ በግራ እጁ መዞ በንጉሡ ሆድ ውስጥ ሻጠ፤


跟着我们:

广告


广告