መሳፍንት 3:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 የእስራኤል ሕዝብ እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረጉ፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር የሞአቡን ንጉሥ ዔግሎንን ከእስራኤል ይበልጥ የበረታ እንዲሆን አደረገው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ይህን በማድረጋቸውም እግዚአብሔር የሞዓብ ንጉሥ ዔግሎን በእስራኤል ላይ እንዲበረታባቸው አደረገ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ይህን ክፋት በጌታ ፊት በማድረጋቸው፥ ጌታ የሞዓብ ንጉሥ ዔግሎን በእስራኤል ላይ እንዲበረታባቸው አደረገ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎምን በእስራኤል ላይ አበረታባቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎምን በእስራኤል ላይ አበረታባቸው። 参见章节 |