መሳፍንት 21:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እነርሱ እንዲህ አሉ፦ “ከእስራኤል ነገዶች መካከል ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ያልመጣ አለን?” እነሆ ከያቤሽ ገለዓድ ወደ ስብሰባው ማንም አልመጣም ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ከዚያም፣ “ከእስራኤል ነገዶች ምጽጳ ላይ በእግዚአብሔር ጉባኤ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን ነው” ሲሉ ጠየቁ፤ ታዲያ ከኢያቢስ ገለዓድ አንድም ሰው ለጉባኤው ወደ ሰፈሩ አለመምጣቱን ተረዱ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ከዚያም፥ “ከእስራኤል ነገዶች ምጽጳ ላይ በጌታ ጉባኤ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን ነው” ሲሉ ጠየቁ፤ ታዲያ ከያቤሽ ገለዓድ አንድም ሰው ለጉባኤው ወደ ሰፈሩ አለመምጣቱን ተረዱ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 እነርሱም፥ “ከእስራኤል ነገድ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ ያልወጣ ማን ነው?” አሉ። እነሆም፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባኤው ማንም አልወጣም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 እነርሱም፦ ከእስራኤል ነገድ ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ያልወጣ ማን ነው? አሉ። እነሆም፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባኤ ማንም አልወጣም ነበር። 参见章节 |