Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 21:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ወደ እናንተ መጥተው ሊቃወሙአችሁ ቢፈልጉ ‘ሚስቶች ለማድረግ የወሰድናቸው በጦርነት አስገድደን ስላልሆነ እባካችሁ ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም በፈቃዳችሁ ስላልሰጣችሁን መሐላችሁን በማፍረስ በደለኞች አትሆኑም’ ብላችሁ መልስ መስጠት ትችላላችሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ቢቃወሙ፣ ‘በጦርነት ጊዜ ለእያንዳንዳቸው የሚሆኑ ሚስቶች ስላላገኘን ነውና እነርሱን በመርዳት ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም ደግሞ ልጆቻችሁን ፈቅዳችሁ ያልዳራችሁ በመሆናችሁ በደለኞች አትሆኑም’ እንላቸዋለን።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ቢቃወሙ፥ ‘በጦርነት ጊዜ ለእያንዳንዳቸው የሚሆኑ ሚስቶች ስላላገኘን ነውና እነርሱን በመርዳት ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም ደግሞ ልጆቻችሁን ፈቅዳችሁ ያልዳራችሁ በመሆናችሁ በደለኞች አትሆኑም’ እንላቸዋለን።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሊጣ​ሉ​አ​ችሁ ወደ እኛ በመጡ ጊዜ፦ ስለ እኛ ማሩ​አ​ቸው፥ እኛ ሚስት ለያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በሰ​ልፍ አል​ወ​ሰ​ድ​ን​ላ​ቸ​ው​ምና፥ እና​ን​ተም በደል ይሆ​ን​ባ​ችሁ ስለ ነበር አላ​ጋ​ባ​ች​ኋ​ቸ​ው​ምና፥” እን​ላ​ቸ​ዋ​ለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አባቶቻቸውና ወንድሞቻቸውም ሊጣሉአችሁ ወደ እኛ በመጡ ጊዜ፦ ስለ እኛ ማሩአቸው፥ እኛ ሚስት ለያንዳንዳቸው በሰልፍ አልወሰድንላቸውምና፥ እናንተም በደል ይሆንባችሁ ስለ ነበረ አላጋባችኋቸውምና፥ እንላችኋለን።

参见章节 复制




መሳፍንት 21:22
10 交叉引用  

በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎም ፈጠራቸው።


ዝናቡ መዝነብ በጀመረበት ቀን፥ ኖኅና ሚስቱ ከልጆቻቸው ከሴም፥ ከካም፥ ከያፌትና ከሦስቱም ልጆቻቸው ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገቡ።


በኋላ እንዳትጸጸት ለእግዚአብሔር ከመሳልህ በፊት ተጠንቅቀህ አስብ።


ነገር ግን ከዝሙት ለመራቅ እያንዳንዱ ወንድ የራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዱዋም ሴት የራስዋ ባል ይኑራት።


እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ “ከእኛ መካከል ማንም ሰው ሴት ልጁን ለብንያማዊ መዳር የለበትም” በማለት ተማምለው ነበር።


ብንያማውያንም ተመልሰው መጡ፤ ሌሎቹም እስራኤላውያን ከሞት በመትረፍ ከያቤሽ ተማርከው የመጡትን ልጃገረዶች ሰጡአቸው፤ ነገር ግን ቊጥራቸው ተመጣጣኝ ሆኖ አልተገኘም።


ይሁን እንጂ ከእኛ መካከል ማንም ሰው ሴት ልጁን ለብንያማዊ ቢድር የተረገመ እንደሚሆን በመሐላ ቃል የገባን ስለ ሆነ ሴቶች ልጆቻችንን ያገቡ ዘንድ ልንፈቅድላቸው አንችልም።”


ከሴቶች ልጆቻችን ማንኛይቱንም ለእነርሱ እንዳንድር በመሐላ ቃል ስለ ገባን ከሞት የተረፉት ብንያማውያን ሚስት ያገኙ ዘንድ ምን እናድርግ?” አሉ።


跟着我们:

广告


广告